Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አገልግሎትና ተደራሽነትን የሚመጥን የአቪዬሽን ደህንነት ዘርፍ ሪፎርም መካ | AddisWalta - AW

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አገልግሎትና ተደራሽነትን የሚመጥን የአቪዬሽን ደህንነት ዘርፍ ሪፎርም መካሄዱ ተገለጸ

ሚያዝያ 21/2015 (ዋልታ) እያደገ የመጣውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አገልግሎትና ተደራሽነት በሚመጥን ደረጃ የአቪዬሽን ደህንነት ዘርፉን ለማጠናከር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ስር የሚገኘውና እንደ አዲስ የተደራጀው የሲቪል አቪዬሽን ደህንነት ዋና መምሪያ የሪፎርም ሥራዎች በከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች እና በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከፍተኛ የሥራ አመራሮች ተጎብኝቷል።

በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ እንደገለጹት፤ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ከአቪዬሽን ደህንነት ጋር በተያያዘ የሚታዩ ውስንነቶችን በተመለከተ ሰፊ ጥናት አድርጓል፡፡

https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid023GQt7DAyFfP54DsSA8FTJG7fKgU1R5heQTrZbcPcKEYMuP6NdP4MtGeDSHN6tQJJl