Get Mystery Box with random crypto!

የዋልታ አመራሮች እና ሰራተኞች የመቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማህበርን ጎበኙ ሚያዝያ 21/2015 ( | AddisWalta - AW

የዋልታ አመራሮች እና ሰራተኞች የመቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማህበርን ጎበኙ

ሚያዝያ 21/2015 (ዋልታ) የዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት አመራሮች እና ሰራተኞች የመቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማህበርን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት የኮርፓሬቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሙሀመድ ሀሰን እንደገለፁት ማህበሩ የወደቁትን በማንሳት እና በመደገፍ ረገድ የሀገር ባለውለታ በመሆን ትልቅ ድርሻ እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።

መቄዶንያን መደገፍ የሁሉም ኃላፊነት ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፓሬት እንደ ከዚህ ቀደሙ በነፃ የሚዲያ አጋር በመሆን አና የተቋሙን ሰራተኞች በማስተባበር ቀጣይነት ያለው እገዛ እናደርጋለን ብለዋል።

የመቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማህበር መስራችና ስራ አስኪያጅ ቢንያም በለጠ በበኩላቸው ዋልታ ሚዲያ ከዚህ ቀደም ላደረጋቸው ድጋፎች በማመስገን በቀጣይ አብራችሁን ለመስራት ፍቃደኛ ስለሆናችሁ እናመሰግናለን ብለዋል።

በመጨረሻም ኮርፓሬቱ ለማህበሩ የአልባሳት ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ሌሎች ድጋፎችንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

በብርቱካን መልካሙ