ያለፉት 5 ዓመታት የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ጉዞ በቴዎድሮስ ሳህለ መጋቢት 23/2015 (ዋልታ) ዲ | AddisWalta - AW

Picture 1 from WALTA TV 2023-04-01 17:10:36
ያለፉት 5 ዓመታት የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ጉዞ

በቴዎድሮስ ሳህለ

መጋቢት 23/2015 (ዋልታ) ዲፕሎማሲ በአገራትና መንግሥታት እንዲሁም በዓለም አቀፍ ተቋማት መካከል የሚካሄድ ዘርፈ ብዙ የውጭ ግንኙነቶች የሚከወኑበት ሁነኛ ጥበብ ነው። የዲፕሎማሲ ዋና ተግባር በአገራት መካከል ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን ማስተዳደር እና ሰላማዊ ግንኙነትን ማረጋገጥ ሲሆን የንግድ ስምምነት ድርድሮችን፣ በጋራ ችግሮች ዙሪያ ውይይትን፣ አዳዲስ ፖሊሲዎች መተግበርን እና አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታትን ያካትታል፡፡ ኢትዮጵያም የሺ ዓመታት ዲፕሎማሲ ልምድ እንዳላት አገር ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር ስትጠቀምበት ቆይታለች፡፡

በኢትዮጵያ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ባለፉት አምስት ዓመታት የገጠሟትን ዓለም አቀፍ ጫናዎችን ለመቋቋም፣ ኢኮኖሚያዊ ግቦቿን ለማሳካት፣ ከአገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር ለመስራት ዲፕሎማሲን በሰፊው እየተጠቀመች ነው፡፡ በዚህም በርካታ ዲፕሎማሲያዊ ሁነቶች ተከስተዋል፡፡ በዘርፉ የውጭና የውስጥ ተግዳሮቶችን በመቋቋም በርካታ ውጤታማ ስራዎች ተሠርቷል፡፡ ለዘህም ውጤት ለውጡን ተከትሎ መንግስት በውጭ ግንኙነት ዙሪያ የወሰደው የፖሊሲ፣ የአሰራር እና የአቅጣጫ እርምጃዎች ምክንያት ሊሆኑ እንደሚችሉ መገመት አያዳግትም፡፡

በአምስት ዓመታት ዓበይት ተግባራት እና ሁነቶች መካከል በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ፣ በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ፣ በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን መድረክ ግንኙነት እንዲሁም በሌሎች ውጤታማ ተግባራት እንደተከናወኑ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ ተጨማሪውን ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡-
https://bit.ly/3KmVYPI
AddisWalta - AW

AddisWalta - AW

@waltatveth
47.51K ተመዝጋቢዎች
ዜና ምድብ
This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel. For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.yout...