Get Mystery Box with random crypto!

ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አ.ማ. በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ የተጋቡ የኬሚካል ጄሪካ | Walia tender ( ጨረታ )

ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አ.ማ. በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ የተጋቡ የኬሚካል ጄሪካኖች ፣ ቆርኪ ካርቶኖች እና ማዳበሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Opens On: Aug 26, 2022
Closes On: Aug 26, 2022
Region: Addis Ababa
Source: አዲስ ዘመን ነሐሴ 14, 2014

የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር፡ ሐቢፋ/01/0138/2022

ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አ.ማ. በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ የተጋቡ የኬሚካል ጄሪካኖች ፣ ቆርኪ ካርቶኖች እና ማዳበሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ፣

አዲስ አበባ ቦሌ ኤድናሞል ወረድ ብሎ ሐርመኒ ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አ.ማ. ዋና መ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
የንብረቶቹን ሁኔታ እስከ ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው ቦታ በመገኘት ማየት ይችላሉ።
ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ድረስ በዋና መ/ቤት በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች ያቀረቡትን የመወዳደሪያ ጠቅላላ ዋጋ 20% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ. በማዘጋጀት ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ጨረታው ነሐሴ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. በ4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዛኑ ዕለት በ 4፡45 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 667 1915 በመደወል ወይም የጨረታ ሠነዱን በማንበብ መረዳት ይቻላል።
አድራሻ

ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አ.ማ. ዋና መ/ቤት

ቦሌ ኤድናሞል ሐርመኒ ሆቴል ፊት ለፊት

ስ.ቁ. 011 667 19 15

አዲስ አበባ

ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አ.ማ.