Get Mystery Box with random crypto!

የሃይማኖት ንጽጽር ኮርስ በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር'Wahid islamic apologetic | ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

የሃይማኖት ንጽጽር ኮርስ

በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር"Wahid islamic apologetics society" 11ኛ ዙር የሙቃረናህ ደርሥ!

"ሙቃረናህ" مُقَارَنَة የሚለው ቃል "ቃረነ" قَارَنَ ማለትም "አነጻጸረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ንጽጽር" ማለት ነው፥ ሙቃረናህ የሃይማኖት ንጽጽር"Comparative Religion" ሲሆን በእሥልምና እና በክርስትና መካከል ያለው የሥነ-መለኮት አንድነት እና ልዩነት እየተነጻጸረ የሚቀርብበት ጥናት ነው። ደርሡ (ትምህርቱ) የሚፈጀው 7 ወር ኢንሻሏህ ሲሆን ሁለት ተርም አለው።

፨ የመጀመሪያው ተርም ዐጽመ አሳብ በፈጣሪ እሳቦት ላይ የሚያውጠነጥነው፦
በሥላሴ"trinity" እሳቤ፣
በነገረ-ክርስቶስ ጥናት"Christology"፣
በነገረ-ማርያም ጥናት"Mariology"፣
በነገረ-መላእክት ጥናት"angelology"፣
በነገረ-ምስል ጥናት"Iconlogy" ላይ ነው።

፨ የሁለተኛው ተርም ዐጽመ-አሳብ በቅዱሳን መጽሐፍት ላይ የሚያውጠነጥነው፦
በአህሉል ኪታብ"People of the Book"፣
በመጽሐፍት"scriptures"፣
በመጽሐፍ አጠባበቅ"preservation"፣
በመጽሐፍት ልኬት"Standardization"፣
በባይብል ግጭት"Contradiction"፣
በኦሪት"Torah"፣
በወንጌል"Gospel" ላይ ነው።

አባሪ ኮርሶች፦
1. ዐቂዳህ"creed"
2. ሥነ ምግባር"ethics"
3. ሥነ አመክንዮ"logic"
4. ሥነ ልቦና"psychology"
5. ሥነ ቋንቋ"linguistics" ናቸው።

ለመመዝገብ ከታች የተዘረዘሩት አድሚናት በውስጥ ያናግሩ!
ወንድም አቡ ኑዓይም፦https://t.me/arhmanu
እኅት ሰላም፦ http://t.me/SeuweSe
አኅት ዘሃራ፦ https://t.me/Zhara_mustefa
እኅት አበባ፦ http://t.me/selemtewa

ቦታ ሳይያዝ ይመዝገቡ! መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልዎ!
ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!