Get Mystery Box with random crypto!

እዚህ አንቀጽ ላይ 'ይበልጣል' ለሚለው የገባው ቃል 'ሜይዞን' μεῖζόν ሲሆን በላጩ አብ ሲሆን | ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

እዚህ አንቀጽ ላይ "ይበልጣል" ለሚለው የገባው ቃል "ሜይዞን" μεῖζόν ሲሆን በላጩ አብ ሲሆን ተበላጩ ደግሞ ሁሉም ነው፥ ኢየሱስ አብ ስላልሆነ "ሁሉ" በሚል ቃላት ውስጥ ኢየሱስ ስለሚካተት አብ ኢየሱስን በባሕርይ ይበልጠዋል። ኢየሱስ፦ "ከ"እኔ" አብ ይበልጣል" ብሏል፦
ዮሐንስ 14፥28 "ከ"እኔ" አብ ይበልጣልና። ὁ Πατὴρ μείζων μού ἐστιν.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ይበልጣል" ለሚለው የገባው ቃል "ሜይዞን" μείζων ሲሆን በላጩ አብ ሲሆን ተበላጩ ደግሞ ኢየሱስ ነው፥ "ከ" የሚለው መስተዋድድ መነሻ ቅጥያ የሆነለት "እኔ" የሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም የኢየሱስ ሙሉ "እኔነትን" ቁልጭ አርጎ ያሳያል፦
ዕብራውያን 2፥7 ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አሳነስኸው። ἠλάττωσας αὐτὸν βραχύ τι παρ’ ἀγγέλους,

"ኤላሶን" ἐλάσσων ማለት "ማነስ" ማለት ሲሆን "ሜይዞን" μείζων ለሚለው ተቃራኒ ነው፥ ኢየሱስ ከመላእክት ያነሰው በባሕርይ ከሆነ ይልቁኑ ከአብ በባሕርይ ምንኛ ያንስ ይሆን?
"ኬኖሲስ" κένωσις የሚለው የግሪክ ኮይኔ ቃል "ኬኖ" κενόω ማለትም "ባዶ አደረገ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ከንቱነት" "ባዶነት"emptiness" ማለት ነው፦
ፊልጵስዩስ 2፥7 ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን "ባዶ አደረገ"። ἀλλὰ ἑαυτὸν ἐκένωσεν μορφὴν δούλου λαβών, ἐν ὁμοιώματι ἀνθρώπων γενόμενος· καὶ σχήματι εὑρεθεὶς ὡς ἄνθρωπος

እዚህ አንቀጽ ላይ "ባዶ አደረገ" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ "ኤኬኖሴን" ἐκένωσεν ሲሆን ሥርወ-ቃሉ "ኬኖ" κενόω ነው፥ "ባዶ አደረገ" የሚለውን አንዳንድ የፕሮቴስታንት አንጃ እና ጎጥ፦ "አምላክነቱን ትቶ መጣ" በሚል ይረዱታል። አምላክነት የሆነ ቦታ አስቀምጠህ የምትመጣበት ጃኬት አይደለም፥ መጨመር እና መጉደል የፍጡር እንጂ የመለኮት ባሕርይ አይደለም። ነገር ግን እንደ ጳውሎስ ትምህርት ኢየሱስ ሕይወቱን በመስጠት ለሰው ልጆች ሲል ድሀ ሆነ ይለናል፦
2 ቆሮንቶስ 8፥9 የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ አውቃችኋልና ሀብታም ሲሆን እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች ትሆኑ ዘንድ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ።

"ቸር ስጦታ" የተባለው ሕይወቱን መስጠቱን እንደሆነ ብዙ ቦታ ተናግሯል፦ ገላትያ 1፥4 ቲቶ 2፥14 ተመልከት! "ራሱን ባዶ አደረገ" ማለት "ራሱን አሳልፎ ሰጠ" ማለት ነው፥ ሕይወትን አሳልፎ ከሰጠ ትልቁ ድህነት(ባዶነት) ነው።
"የባሪያ መልክ" ማለት "ባርነት" ማለት ነው፥ ለምሳሌ "የአምልኮ መልክ" ማለት "አምልኮት" ማለት ነው፦
2 ጢሞቴዎስ 3፥5 የአምልኮት "መልክ" አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ። ἔχοντες μόρφωσιν εὐσεβείας τὴν δὲ δύναμιν αὐτῆς ἠρνημένοι· καὶ τούτους ἀποτρέπου.

"ሞርፎሲስ" μόρφωσις ወይም "ሞርፌ" μορφή የሚሉት ቃላት "ሞርፎ" μορφόω ከሚል ግሥ መደብ የመጣ ሲሆን "መልክ"form" ማለት ነው፥ ኢየሱስ ባርነት ይዞ እራሱን አዋረደ፦
ፊልጵስዩስ 2፥8 በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ። ἐταπείνωσεν ἑαυτὸν γενόμενος ὑπήκοος

ኢየሱስ፦ "ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል" ብሎ ባስተማረው መሠረት ራሱን በትህትና በማዋረዱ አምላክ ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፦
ማቴዎስ 23፥12 ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል። καὶ ὅστις ταπεινώσει ἑαυτὸν ὑψωθήσεται.
ፊልጵስዩስ 2፥9 በዚህ ምክንያት ደግሞ አምላክ ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው። διὸ καὶ ὁ Θεὸς αὐτὸν ὑπερύψωσεν,

ከመላእክት ያሳነሰው እና እራሱን በማዋረዱ ከፍ ከፍ ያደረገው አንዱ አምላክ ከሆነ አንዱ አምላክ እና ኢየሱስ ሁለት ለየቅል ማንነት እና ምንነት ይሆናሉ፥ በምንነት ከተለያዩ ኢየሱስ ከአምላኩ ጋር በባሕርይ ሊስተካከል አይችልም። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም