Get Mystery Box with random crypto!

#የሰው_ነፃ_ፍቃድና_አወዳደቁ ነፃ ፍቃድ ስንል ምን ማለታችን ነው ? ሰውን ሲፈጥረው የሚያስብና | ማህበር ሐዋርያት ቢሊዳ ማርያም

#የሰው_ነፃ_ፍቃድና_አወዳደቁ

ነፃ ፍቃድ ስንል ምን ማለታችን ነው ?

ሰውን ሲፈጥረው የሚያስብና የሚያስተውል ሆኖ ነው ። ከዚህም የተነሳ ክፉውንና በጎን ማወቅ የሚችልበት አእምሮና ከሁለት አንዱን መርጦ እንዲጓዝ ነፃነት አለው ።እግዚአብሔር አዳምን ከፈጠረው ቡሃላ የሚጠቅመውንና የሚጎዳውን ነግሮ በገነት አኑሮታል

ከዚህም ቡሃላ የሚበጀውን መምረጥ የእርሱ ድርሻ ነበር
በሕይወት ለመኖርም ሆነ ለመሞት መወሰን በእጁ ነው። እንግዲህ ይህ ነው የሰው ልጅ #ነፃ_ፍቃድ የሚባለው ። እናም አዳም ነፃ ፍቃዱን ተጠቅሞ እጸ በለስን በላ በዚህም ወደቀ

#የሰው_ልጅ_ውድቀት_ስንል_ምን_ማለታችን_ነው ?

#1ኛ .ራቁታቸውን ሆኑ ። ለነርሱ ልብስ አልነበራቸውም ነገር አይተፋፈሩም ነበር ። የፀጋ ልብስ ነበራቸው ። #2ኛ .ኃይላቸውን አጡ ፦ ይህም ሲባል ሀጢአት የሰውን ኃይል ያሳጣልና #3ኛ .ሰላማቸውን አጡ

#4ኛ .ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቸው ግንኙነት ተቋረጠ ። #5ኛ .መርገም አመጡ ። #ሀ ነፃነታቸውን አጡ ። ሞትን ወይም ህይወትን የመምረጥ መብት ነበራቸው ኀላ ግን ሞትን ተቀብለው ነፃነታቸውን አጡ ባሪያ ሆኑ ። #ለ ሕይወታቸውን አጡ

ቀድሞ ለዘላለም ይኖሩ ዘንድ ተሰጥቷቸው ነበር ኀላ ግን በበደላቸው ሞት መጣባቸው ህይወታቸውንም አጡ። #ሐ የገነት በር ተዘጋባቸው ። #መ ባለ ዕዳ ሆኑ ። ማንም ሊከፍለውም የማይችለውን የሞት ባለዕዳ ሆኑ ። ይህንንም እዳ #ከኢየሱስ_ክርስቶስ በቀር ትውልድ ሙሉ ሊከፍሉት አይችልም

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
•➢ ሼር // SHARE

•✥• @Amda_Hayimanot •✥•
•✥• @Amda_Hayimanot •✥•
•✥• @Amda_Hayimanot •✥•