Get Mystery Box with random crypto!

ልዩ ጥያቄ መልስ ውድድር እውነት / ሀሰት 1. መጥምቁ ዮሀንስ በይሁዳ ምድረ በዳ ነበር | ማህበር ሐዋርያት ቢሊዳ ማርያም

ልዩ ጥያቄ መልስ ውድድር

እውነት / ሀሰት

1. መጥምቁ ዮሀንስ በይሁዳ ምድረ በዳ ነበር እየሰበከ የመጣው

2. ሄሮድስ ጌታችን በምን ዘመን እና የት እንደሚወለድ ያረጋገጠው ህዝቡን ጠርቶና ጠይቆ ነው

3. ዮሴፍ እመቤታችንን በስውር ሊተዋት ሲል የእግዚአብሔር መልአክ በህልም ታየው።

4. አብረሀም ይስሐቅን ወለደ ይስሐቅም ዮሴፍን ወለደ።

5. "ሴትን አይቶ በልቡ የተመኛት ሁሉ አመነዘረባት።"

6. "አንድ ምዕራፍ ትሄድ ዘንድ ቢያስገድድህ አንድ ምዕራፉን ያህል ሂድለት።"

7. የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም።

8. "በወንድሙ ላይ በከንቱ የሚቆጣ ሁሉ እርሱ ይፈረድበታል።"

9. ዲያቢሎስ ጌታችንን ለሶስተኛ ጊዜ የፈተነው በፍቅረ ነዋይ ነው።

10. ጌታችን ኦሪትንና ነቢያትን ሊሽር ነው የመጣው።

ምርጫ

11. ሰብዓ ሰገል ጌታችንን ካገኙ በኋላ ወደ ሄሮድስ እንዳይመለሱ በምን ተረዱ

ሀ/ በህልም ተነግሯቸው
ለ/ በቀጥታ ተነግሯቸው
ሐ/ ልቦናቸው ስላልወደደ
መ/ መልስ የለም

12. የጌታ መልአክ ለዮሴፍ ተገልጦ "ህፃኑን ሊገድሉት የሚወዱት ሞተዋልና ህፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ___ሂድ።"

ሀ/ ወደ ሶሪያ
ለ/ ወደ ግብፅ
ሐ/ ወደ እስራኤል
መ/ መልስ የለም

13. እኔ ግን እላችኋለሁ ጠላቶቻችሁን

ሀ/ አትጥሉ
ለ/ ውደዱ
ሐ/ ጥሉ
መ/ ተበቀሉ

14. አርኬላዖስ ማን ነው

ሀ/ ከሰብዓ ሰገል አንዱ
ለ/ የሄሮድስ ወታደር
ሐ/ የጌታችን ሀዋርያ
መ/ የሄዶድስ ልጅ

15. ልጅም ትወልዳለች እርሱም ህዝቡን ከሀጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን_ ትለዋለህ

ሀ/ አማኑኤል
ለ/ ኢየሱስ
ሐ/ መድሀኚአለም
መ/ መልሱ አልተጠቀሰም

16. ጌታችን በዲያቢሎስ የተፈተነው ስንት ጊዜ ነው?

ሀ/ 2
ለ/ 3
ሐ/ 4
መ/ 5

17. ለሚለምንህ ሁሉ ____።

ሀ/ አበድር
ለ/ እዘን
ሐ/ ስጥ
መ/ መልስ የለም

18. ጌታችን ወደ ዮሀንስ ሊጠመቅ በመጣ ሰአት ዮሀንስ ምንድን ነበር ያለው።

ሀ/ ጌታዬ በፊትህ ሞገስን አግኝቼ በእኔ ዘንድ ልትጠመቅ በመምጣትህ አመሰግናለሁ

ለ/ እኔ በአንተ ልጠመቅ ይገባኛል አንተ እንዴት ወደ እኔ ትመጣለህ

ሐ/ ምንም አላለውም

መ/ መልስ የለም

19. ሰብዓ ሰገል ከየትኛው አቅጣጫ ነበር የመጡት?

ሀ/ ከምስራቅ
ለ/ ከምዕራብ
ሐ/ ከሰሜን
መ/ ከደቡብ

20. ሄሮድስ ሰብዓ ሰገል እንደዘበቱበት በተረዳ ጊዜ ምን አደረገ

ሀ/ በጭፍራዎቹ አሳዶ ገደላቸው
ለ/ ወደ ሄዱበት ስፍራ ሄደ
ሐ/ ህፃናትን አስገደለ
መ/ ምንም አለደረገም

ዳሽ ሙላ

21. እናንተ የምድር_ናችሁ።

22. ነገር ግን ቃላችሁ__ወይም__ ይሁን።

23. ተከተሉኝ ሰውን_ አደርጋችኋለሁ።

24.እኔ ግን እላችኋለሁ ክፉን በክፉ ____።

25. ፅድቃችሁ ከ እና ጽድቅ ካልበለጠ መንግስተ ሰማይ አትገቡም።

ፃፉ

26. ገሀነመ እሳት የሚያስገባ ስድብ ምንድን ነው?

27. የያዕቆብና የዮሀንስ አባት ስሙ ማን ነው?

28. ዮሴፍ እመቤታችንንና ጌታችንን ወደ የት ሀገር ይዞ ሸሸ?

29. የትውልድ ዘመን ቁጥር በየትኛው ምዕራፍ ላይ የተገለጠ ነው?

30. እስከ ዛሬ ባለው ትረካዊ ትምህርት ምን ምን ተረዳችሁ?

ለበረከቱ ሁላችሁም ተሳተፉ

መልስ መስጫ @Yb_19bot

ቻናላችንን ለመቀላቀል @betekrstiyan_21

(መልሶቻችሁን ስታስገሙ የክርስትና ስማችሁ ቀድማችሁ መፃፉን አትርሱ)