Get Mystery Box with random crypto!

ፋኖ #መሰረት በላይ በምስራቅ ጎጃም ተገደለ ከአንድ ሻለቃ የማያንስ ጦር ዘምቶበት ነበር / ፋኖ | የ አማራው ድምፅ (ፋኖ)

ፋኖ #መሰረት በላይ በምስራቅ ጎጃም ተገደለ

ከአንድ ሻለቃ የማያንስ ጦር ዘምቶበት ነበር

/
ፋኖ መሰረት በላይ በምስራቅ ጎጃም ከሚያሳድዱት የመንግሥት ታጣቂዎች ጋር እየተዋጋ ከቆየ በኋላ፣ ጥይት ሲያልቅበት ባለፈው አርብ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም. መሰዋዕቱን ቤተሰቦቹ አረጋገጡ። ወደ ፋኖ መሰረት በላይ የዘመተው ከአንድ ሻለቃ ጦር የማያንስ እንደሆነም ታውቋል።

ከተሰዋ በኋላ ገዳዮቹ የእግሩን ጫማ አውልቀው ወስደውታል። በተጨማሪም፣ በኪሱ ውስጥ ያገኙትን ተንቀሳቃሽ ስልክና ገንዘብ ወስደውታል። የዘመዶቹን ቤቶች እየተዘዋወሩ ከበረበሩ በኋላ በሞራላቸው ላይም ተሳልቀዋል።

መሰረት ባለትዳርና በንግድ ሥራ ላይ ተሠማርቶ የነበር ሲሆን፣ በቅርቡ የአማራ ሕዝባዊ ኃይልን (ፋኖ) ተቀላቅሏል።

ይህ በአንዲህ እያለ፣ ባሕር ዳር ከተማ፤ ቀበሌ 14 አኮቴት አደባባይ አካባቢ የሚገኘው የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) መጋዝን ትላንት ማክሰኞ፤ ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ በመንግስት ኃይሎች ተይዟል። በውስጡ የነበሩ የፋኖ አልባሳትን እና ምግቦች በመኪና ተጭነው ባሕር ዳር ዘጠነኛ ፖሊስ ጣቢያ ገብተዋል።

ድርጊቱ በአካባቢው ኗሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ቁጣና ብስጭትን ፈጥሯል።

#ጀግና ታግሎ ይሰዋል የጀመረው ትግል ይቀጥላል በወንድሞቹ ድል አድራጊነት ይደመደማል

https://t.me/voice_of_amhara_FANO