Get Mystery Box with random crypto!

Voa Amharic

የቴሌግራም ቻናል አርማ voaamharic — Voa Amharic V
የቴሌግራም ቻናል አርማ voaamharic — Voa Amharic
የሰርጥ አድራሻ: @voaamharic
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.27K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ voa amharic ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-04-01 18:05:16
ሩስያ ከዛሬ በኋላ በሩስያ ገንዘብ ሩብል ካልሆነ ጋዝ አልሸጥም ብላለች


የአውሮጳ ኅብረት በሩስያ ጋዝ አቅርቦት ቀነ-ገደብ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል።


የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ከዛሬ ጀምሮ ጋዝ እና ነዳጅ ከሩስያ የመገበያያ ገንዘብ ሩብል ውጪ እንደማይሸጡ ማስጠንቀቃቸው አውሮጳውያንን አስጨንቋል። ፑቲን፦ «ወዳጅ ያልሆኑ» ያሏቸው ሃገራት የአውሮጳ ኅብረትን ጨምሮ ከሩስያ ጋዝ መግዛት ከፈለጉ በሩብል እንጂ በዶላር አለያም በዩሮ አንሸጥም ሲሉ ቀደም ሲል አስጠንቅቀዋል። ሃገራቱ ከሩስያ ጋዝ መግዛት ከፈለጉም የሩስያ መንግሥት በሚቆጣጠረው ጋዝፕሮም ባንክ በሩብል ሒሳብ አካውንት መክፈት እንደሚገባቸውም ተናግረዋል።

አውሮጳውያን ነዳጅ መግዛት ሲፈልጉም በቀጥታ በሩብል ለሩስያ እንዲከፍሉ ያስገድዳል አዲሱ የሩስያ አስገዳጅ ጥያቄ። የአውሮጳ ኅብረት ሃገራት እና ኩባንያዎች በሩስያ የተሰጠው ቀነ ገደብ ዛሬ ከማለፉ በፊት የጋራ አቋም ለመያዝ መመምከራቸው ተገልጧል። የጋዝ አቅርቦቱ እንዳይቋረጥበት ስጋት የገባው የጀርመን መንግሥት ሩስያ ጋዝ በሩብል ነው የምሸጠው ማለቷን በተመለከተ ጉዳዩን «ሲመረምረው እንደነበር» ዐስታውቋል።

አውሮጳ 40 ከመቶ የጋዝ አቅርቦቱ የሚሸነፈው ከሩስያ ከሚገኝ ኃይል ነው። እናም ሩስያ የነዳጅ አቅርቦቱን ብታቋርጥ፦ ግዙፍ ፋብሪካዎች እንዲዘጉ በማስገደድ የኃይል አቅርቦት ዋጋ እጅግ በጣም ይጨምራል።

የሩስያ መገበያያ ገንዘብ «ሩብል» የአምስት ሳምንት ከፍተኛ ጣራውን በመንካት ከፍ ማለቱ ተዘግቧል። የሩስያ አክሲዮን ገበያ ዛሬ ከፍ ያለ ሲሆን፤ 1 ዶላር ከ83-84 ሩብል እንደሚቀየርም ተገልጧል። ከ9 ቀናት በፊት 1 ዶላር የሚመነዘረው በ106 ሩብል ግድም ነበር።

https://www.facebook.com/dw.amharic/posts/5465504080149310
3.3K views15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 18:05:16 …ግራ ቀኙን የተመለከተው የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የሥር ፍርድ ቤቱ የሰጠውን የዋስትና መብት በመሻር፣ ተከሳሾቹ ለተጨማሪ 10 ቀናት እሥር ቤት ሆነው ፖሊስ ምርመራውን እንዲያካሄድ ትዕዛዝ መስጠቱንም ፓርቲው አክሎ ገልጿል፡፡


ዘገባ፦ ሰለሞን ሙጬ፤ ዶይቸ ቬለ (DW)ከአዲስ አበባ
ፎቶ፦ ከባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ የፌስቡክ ገጽ የተወሰደ።
2.3K views15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 18:05:16
ባልደራስ፦ የታሰሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች ዋስትና መሻሩን ገለጠ

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በቁጥጥር ሥር የዋሉና ትላንት ዋስትና ተፈቀዶላቸው የነበሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች ዛሬ ዋስትናቸው መሻሩን ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ገለፀ።
ፓርቲው እንዳስታወቀው፦ ከአድዋ ድል ክብረ በዓል አከባበር ጋር በተገናኘ በእሥር ላይ ካሉት ወጣቶች መካከል የተወሰኑት ትናንት የዋስትና መብት ተፈቅዶላቸው የነበረ ቢሆንም፤ ዛሬ ተጨማሪ 10 ቀናት በእስር ቤት እንዲቆዩ ተወስኗል ብሏል።

በእነ ደረጀ ይበይን መዝገብ ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበሩት የአዲስ አበባ ወጣቶች ትናንት በነበረው ችሎት የ7 ሺህ ብር ዋስ ተፈቅዶላቸው የነበረ ቢሆንም፣ ፖሊስ ከሰዓት በኋላ ይግባኝ በማቅረቡ ጉዳዩ ዛሬ ጠዋት መታየቱን ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ተናግሯል።

ፖሊስ ተከሳሾችን የሚመለከት ምርመራ አለማጠናቀቁን፣ በምርመራ ሂደት ያገኛቸውን ማስረጃዎች በባለሞያዎች እያስተነተነ መሆኑን፣ ይህም ጊዜ የሚጠይቅ መሆኑን በመግለጽ ተጨማሪ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል ያለው ፓርቲው፣ ትናንት የነበረው ችሎት የሰጠውን የዋስትና መብት አግባብ አይደለም በማለት መቃወሙንም ገልጿል፡፡

የተከሳሾች ጠበቆች እስረኞቹ ለ1 ወር የሚጠጋ ጊዜ በእስር ላይ እየተንገላቱ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ፖሊስ በተደጋጋሚ የሚያቀርበው ምክንያትም ተመሳሳይ መሆኑ፤ ምርመራው ከልብ እየተሠራ አለመሆኑን እንደሚያመላክት ተናግረዋል። ጠበቆቹ የተከሳሾቹን በእስር መቆየት እንደማይፈልጉና የዋስትናው መብት ሊከበር እንደሚገባ ገልፀዋል ሲልም ፓርቲው የላከው መረጃ ያሳያል…
https://www.facebook.com/dw.amharic/posts/5465420396824345
2.0K views15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 18:05:16
የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሮመዳን መልእክት


መላው ሙስሊም የሮመዳንን ፆምን ፈጣሪን በመማለድና የተፈናቀሉ ወገኖችን በመርዳት እንዲያሳልፍ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት መከረ።


የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ሸክ ሰዒድ መሐመድ ዛሬ ለዶይቼ ቬሌ (DW) በሰጡት መግለጫ፦ ወቅቱ በአገራችን በተለይም በአማራ ክልል ከፍተኛ መፈናቀል፣ እንግልትና የኑሮ ጉስቁልና የደረሰበት ሙስሊም ኅብረተሰብ በዚህ ቅዱስ የፆም ወር ፈጣሪ ለአገራችን ሰላም እንዲመጣ ዱዓ (ጸሎት) ማድረግ እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡


ሼክ ሰዒድ «በሀገራችን በተቀሰቀሰዉ ጦርነት ምክንያት በርካታ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል፣ የአካባቢ መሰረተ ልማቶችና የጤና ተቋማትና ወድመዋል፣ ከ100 በላይ መስጊዶች ወድመዋል» ብለዋል፡፡


አክለውም «በረመዳን ወር የተፈናቀሉትን ወገኖች በምግብና በአልባሳት በመደገፍ እስካሁን የተደረገውን ድጋፍ በዚህ የፆም ወቅትም አጠናክረን መቀጠል» አለብን ብለዋል። «እንዲሁም በተከሰተው የኑሮ ውድነት ምክንያት ሕይወታቸው የተመሰቃቀለውን ወገኖቻችንን ከምንጊዜውም በላይ መደገፍ፣ ከሳዑዲ አረቢያ ተመላሽ ዜጎቻችንን በገዛ አገራቸው ባየተዋርነት እንዳይሰማቸው ከጎናቸው ልንቆም ይገባል» ሲሉም ጥሪ አስተላልፈዋል።፡


የሀገራችን ችግር የሚፈታው በኢትዮጵያውያን መካከል በሚደረግ ውይይት ነው ያሉት ሸክ ሰኢድ በጫናና በዛቻ እንዳልሆነም ተናግረዋል፡፡ «በመሆኑም HR 6600 እና S 3199 የተባሉ ሰነዶችን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድነትና በቁርጠኝነት መቃወም አለበት» ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
1443ኛው ዓመተ ሂጅራ ታላቁ የሮመዳን ፆም ነገ ወይም እሁድ ይጀምራል፡፡
ዘገባ፦ ዓለምነው መኮንን፤ ዶይቸ ቬለ (DW) ከባሕርዳር
1.3K views15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 13:54:08 …አስተያየታቸውን ለDW የሰጡት ተመላሾች ወደ አገራቸው መመለሳቸው እጅግ እንዳስደሰታቸው ገልፀው፤ በሳውዲ አረቢያ ከፍተኛ እንግልትና ሥቃይ ማሳለፋቸውን እያለቀሱ ጭምር ተናግረዋል። እስከ ዐሥር ወራት ድረስ እና ከዚያም በላይ እሥር ቤት ውስጥ ታጉረው መቆየታቸው፣ በተለይ ወንዶች እስር ቤቶች ውስጥ የባሰ ግፍ እንደሚፈፀምባቸው ገልፀው ይህ ጅምር በችግር ላይ የሚገኙትንም ሳይቆራረጥ እስከማስወጣት እንዲዘልቅም ተማፅነዋል።


ከሳውዲ ተመላሾቹ ሰነዶቻቸው እየታየ ወደ ትውልድ ቀያቸው እንዲመለሱ ይደረጋል ተብሏል። የሚሄዱበት ወገን ዘመድ እኔ ቤተሰብ የሌላቸው ተመላሾች ደግሞ እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ በተዘጋጁ ማቆያ ሥፍራዎች ውስጥ እንደሚቆዩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መናገሩን የአዲስ አበባ ወኪላችን ሰለሞን ሙጬ የላከልን ዘገባ ይጠቁማል። በዛሬው የዜና መጽሄት ዝርዝር ዘገባ ይኖረናል ፤ ጠብቁን።
https://www.facebook.com/dw.amharic/posts/5464926173540434
1.2K views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 13:54:08
ከ1000 በላይ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ


በሳውዲ አረቢያ በተለያዩ እሥር ቤቶች ውስጥ ታስረው በስቃይ እና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን መካከል ከጅዳ ከተማ ዛሬ እስከ እኩለ ቀን ድረስ በተደረጉ ሦስት በረራዎች 1173 ኢትዮያውያን ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ተደረገ።


የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዕንዳስታወቀው ዛሬ ብቻ ከጄዳ 1881 ኢትዮጵያዊያን ወደ አዲስ አበባ ይመለሳሉ።መንግሥት በሳውዲ አረቢያ በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ 102 ሺህ ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ በያዘው እቅድ መሠረት ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ 2111 ኢትዮጵያዊያንን መመለሱን ተናግሯል።እስካሁን ወደ አገራቸው እየተመለሱ ከሚገኙት ኢትዮጵያውያን መካከል አብዛኛዎቹ ሕፃናት፣ ሴቶች እና ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ናቸው ተብሏል።


ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በችግር ላይ ከሚገኙት በርካታ ሺህ ኢትዮጵያዊያን መካክል እስካሁን 45 ሺህ ሰዎች ወደ አገራቸው ለመመለስ መመዝገባቸውም ተገልጿል። ዶይቼ ቬለ (DW) ዛሬ ጥዋት ከጅዳ የተመለሱ ዜጎችን በቦሌ አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ተገኝቶ እንደተመለከተው አብዛኞቹ ተመላሾች ሴቶች ናቸው። ከጥዋቱ አራት ሰዓት ግድም የገቡት እነዚህ ፍልሰተኞችን አጓጉዞ ያመጣው የሳውዲ አረቢያ ንብረት የሆነ ግዙፍ አውሮፕላን መሆኑንም ተመልክተናል። … https://www.facebook.com/dw.amharic/posts/5464926173540434
1.0K views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 13:54:08 ከ1000 በላይ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ


በሳውዲ አረቢያ በተለያዩ እሥር ቤቶች ውስጥ ታስረው በስቃይ እና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን መካከል ከጅዳ ከተማ ዛሬ እስከ እኩለ ቀን ድረስ በተደረጉ ሦስት በረራዎች 1173 ኢትዮያውያን ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ተደረገ።


የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዕንዳስታወቀው ዛሬ ብቻ ከጄዳ 1881 ኢትዮጵያዊያን ወደ አዲስ አበባ ይመለሳሉ።መንግሥት በሳውዲ አረቢያ በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ 102 ሺህ ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ በያዘው እቅድ መሠረት ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ 2111 ኢትዮጵያዊያንን መመለሱን ተናግሯል።እስካሁን ወደ አገራቸው እየተመለሱ ከሚገኙት ኢትዮጵያውያን መካከል አብዛኛዎቹ ሕፃናት፣ ሴቶች እና ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ናቸው ተብሏል።


ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በችግር ላይ ከሚገኙት በርካታ ሺህ ኢትዮጵያዊያን መካክል እስካሁን 45 ሺህ ሰዎች ወደ አገራቸው ለመመለስ መመዝገባቸውም ተገልጿል። ዶይቼ ቬለ (DW) ዛሬ ጥዋት ከጅዳ የተመለሱ ዜጎችን በቦሌ አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ተገኝቶ እንደተመለከተው አብዛኞቹ ተመላሾች ሴቶች ናቸው። ከጥዋቱ አራት ሰዓት ግድም የገቡት እነዚህ ፍልሰተኞችን አጓጉዞ ያመጣው የሳውዲ አረቢያ ንብረት የሆነ ግዙፍ አውሮፕላን መሆኑንም ተመልክተናል...


https://www.facebook.com/dw.amharic/posts/5464926173540434
904 views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 12:38:27
የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ያስከተለዉ ውዝግብ


በኢትዮጵያ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት በተመለከተ በተለይ በአማራ እና ደቡብ ክልሎች ላይ «አሻጥር ተፈጽሟል» በሚል በርካታ ተቃውሞዎች ከሰሞኑ ተሰምተዋል። በጦርነት ውስጥ የነበሩ ተማሪዎችን በአንጻራዊነት ሰላም ካላቸው አካባቢዎች እኩል እንዲፈተኑ ማድረጉም ተገቢ አይደለም የሚሉ ቅሬታዎችም ይደመጣሉ። ይህንኑ በተመለከተ፦ «ትምህርት የሴራ ማስፈጸሚያ አይደለም» የሚሉ መፈክሮች በቅርቡ አማራ ክልል ውስጥ በተለያዩ ከተሞች በተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ ተንጸባርቀዋል። «ሕዝብ በትምህርት ሥርዓቱ ላይ አመኔታ የሚያጣ ከሆነ ተሻጋሪ የሆነ ችግርን ሊያስከትል ይችላል» የሚሉ እና ሌሎች የተቃውሞ መልእክቶችም ተሰምተዋል። የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ማተብ ታፈረ፦ «ትምህርት ሚንስቴር ውጤቶቹን ተንትኖ ፍትሐዊ የሆነ የመቁረጫ ነጥብ መወሰንና ግልጸኝነት የመፍጠር ኃላፊነት አለበት» ሲሉ ተናግረዋል።


በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትና ያስከተለዉ ተቃዉሞ ላይ ያላችሁን አስተያየት አጋሩን። ምንስ ቢደረግ የተሻለ ነገር ሊመጣ ይችላል ትላላችሁ? ተወያዩበት።

https://www.facebook.com/dw.amharic/posts/5464775513555500
851 views09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 12:38:27 የሐሙስ መጋቢት 22 ቀን 2014 ዓም ዐርዕስተ ዜና
የኢትዮጵያ መንግሥት ዛሬ የእርዳታ እህል በየብስ ወደ ትግራይ ክልል መጓጓዝ መጀመሩን አስታወቀ። የኢትዮጵያ መንግሥት የኮምኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው መግለጫ እንዳለው፣ በዓለም ምግብ ድርጅት አማካኝነት የእርዳታ እህል የያዙ 21 ከባድ የጭነት መኪናዎች በአፋር ክልል በአብኣላ መንገድ ወደ ትግራይ ክልል መጓዝ ጀምረዋል ።

የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ የበጀት ኮሚቴ ፣ኢትዮጵያ ውስጥ በተካሄደው ግጭት ተፈጽመዋል የሚባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለሚያጣሩ ገለልተኛ ባለሞያዎች ገንዘብ እንዲመደብ ያቀረበውን ሃሳብ ለማገድ ኢትዮጵያ ባቀረበችው ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ዛሬ ድምጽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ኢትዮጵያ ምክር ቤቱ አዲስ ምርመራ እንዲካሄድ መጠየቁ የከዚህ ቀደሙን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶ ኮሚሽንና የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የጋራ ምርመራ ጥረትሙሉ በሙሉ የሚያንኳስስ ነው ስትል ተቃውማለች ።

ሩስያ «ወዳጅ ያልሆኑ» ያለቻቸው ሀገራት፣ የውጭ ምንዛሬን ወደ ሩብል በሚቀይር የሩስያ ባንክ በኩል ክፍያ በመፈጸም ከሩስያ ጋዝ መግዛት ሊቀጥሉ እንደሚችሉ ዛሬ በደነገገችው አዋጅ አስታወቀች። የሩስያው ፕሬዝዳንት ብላድሚር ፑቲን ዛሬ እንደተናገሩት ደንበኞች ጋዝ ለመግዛት በሩስያ ባንኮች የሩብል ሂሳብ ቁጥር መክፈት አለባቸው።
ሙሉውን ዜና ለማዳመጥ ከታች የሚገነeን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ
https://p.dw.com/p/49IsU
829 views09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 07:34:44 ተቃውሞና ድጋፍ በS 3199 ረቂቅ ሕግ ላይ

የረቂቅ ሕጉ ተቃዋሚዎች በኢትዮጵያ ሰላምና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ለማበረታታት በሚል ርዕስ የተረቀቀው ሕግ የኢትዮጵያን ኤኮኖሚ የሚጎዳና ሀገሪቱ ዓለም አቀፍ ብድርም ሆነ እርዳታ እንዳታገኝ የሚከለክል ነው ሲሉ ለዶቼቬለ ተናግረዋል።መጽደቁን የደገፉ ደግሞ ሕጉ ተጠያቂነትን ያስፍናል ሲሉ ሞግተዋል።
https://p.dw.com/p/49Ego?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot
880 views04:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ