Get Mystery Box with random crypto!

'መጽሐፍ ቅዱስ የተሰጠን ዕውቀት እንድጨምርልን ሳይሆን ህይወታችን እንድለወጥ ነው፡፡' ዲ ኤል | " ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"

"መጽሐፍ ቅዱስ የተሰጠን ዕውቀት እንድጨምርልን ሳይሆን ህይወታችን እንድለወጥ ነው፡፡" ዲ ኤል ሙዲ፡፡

ሁል ግዜ ይህንን አስብ
መጽሐፍ ቅዱስን ካነበብክ፣ ካጠናክ፣ እና ካሰላሰልክ በኃላ አንድ ነገር ማድረግን እንዳትረሳ፤ እሱም፦ ጌታ በቃሉ ምን እንደተናገረህና በህይወትህ እንዴት በተግባር ላይ ማዋል እንደምትችል አስብ፤ ብቻልህ በማስታወሻ ለመጻፍ እና መንፈስ ቅዱስ በምሰጥህ ምሪት መሠረት ተግባራዊ አድርግ፡፡

መንፈሳዊ ዕድገት የምመጣው፣ የጋለና የተቀጣጠሌ መንፈሳዊ ህይወትን መኖር የምትችለው ባነበብከው፣ ባጠናሄው እንድሁም ባሰላሰልከው መጠን ሰይሆን ያነበብከውን ያጠናሄውን እና ያሰላሰልከውን ሁሉ በህይወትህ ላይ ተግባራዊ ባደረከው መጠን መሆኑን ልብ በል፡፡

በነገራችን ላይ ተግባራዊ እስካላደረግነው ድረስ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበባችን ማጥናታችንና ማሰላሰላችን ሰይጣንን አያስጨንቀውም፡፡

ቆሚ ብለህ አስብ!

ተግባራዊ ያልሆኔ የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀትን ማወቅና መጽሐፍ ቅዱስን ምንም አለማወቅ ሁለቱም ዕኩል ናቸው፤ አንድ ናቸው፡፡ ምክንያቱም ሁለቱንም በተግባር ስመዘን ውጤቱ ይሆናል ከመቶ ዜሮ፡፡( 0/100)፡፡

ይህንን ዕርምጃ ወስደን እንድሁም ተግብረን በህይወታችን ፍሬ እንድናፈራ ( 30,60,100) የጌታ ጸጋና ሠላም ምህረቱም ይብዛልን፡፡ ተባርካቿል፡፡



https://t.me/UznesswzChristJesus