Get Mystery Box with random crypto!

ሰው ካለ ሳይኮሎጂ አለ፡፡

የቴሌግራም ቻናል አርማ uog_psych — ሰው ካለ ሳይኮሎጂ አለ፡፡
የቴሌግራም ቻናል አርማ uog_psych — ሰው ካለ ሳይኮሎጂ አለ፡፡
የሰርጥ አድራሻ: @uog_psych
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.45K
የሰርጥ መግለጫ

"የዘመናችን ትልቁ ግኝት የሰው ልጅ አመለካከቱን በመቀየር ህይወቱን መቀየር መቻሉ ነዉ።"

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-17 11:36:38 #የአእምሮ_ህመም_የማይመስሉ_የአእምሮ_ህመሞች

ማህተመ ጋንዲ ከአንድ ሰው ጋር ይጣላል። ጥፋቱ የሰውየው ነው። ማህተመ ጋንዲ ይቅርታ ሊጠይቀው ይሄድና እግሩ ስር ይወድቃል። ሰውየው በእግሩ ፊቱን ይጠልዘዋል። ጋንዲ ጥርሱ ተነቃንቆ ደም በደም ይሆናል። ቀና ብሎ ሰውየውን እየተመለከተ "ወንድሜ ፊቴ እግርህን አልጎዳህም አይደል?" ብሎ ጠየቀው አሉ።

ብዙ ሰው ይህንን ታሪክ ሲሰማ "እንዴት ትሁት ሰው ነው?" ሊል ይችላል። አንዳንድ ሳይካትሪስቶች ደግሞ "Moral masochism" የሚባል ህመም እንዳይሆን ብለው ሊያስቡ ይችላሉ። ማሶኪዝም (Masochism) በፆታዊ ግንኙነት ወቅት ሲገረፉ ብቻ የደስታ ጥግ ላይ የሚደርሱ ሰዎችን ይገልፃል። የሞራል ማሶኪዝም ደግሞ በስቃይና በእንግልት ደስታ የማግኘት ስነ ልቦናዊ ክስተት ነው።

የጋንዲ ጉዳይ አከራካሪ ሊሆን ንችላል። ነገር ግን አንዳንድ ህመም የማይመስሉን ፀባዮች የአእምሮ ህመም ምልክት ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ ከፍተኛ ጥንቃቄ፣ ስራ በጣም መስራት፣ ብዙ እቃ መግዛት፣ መኮላተፍ....ዝርዝሩ ረጅም ነው።

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ከዶ/ር ዮናስ ላቀው
@UoG_Psych
365 views08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 10:14:53 #ሰው_ሁን!

ሰው ከመሆንህ በፊት ዶክተር (ሐኪም) አትሁን፡፡ ሰው ከመሆንህ በፊት መሐንዲስ አትሁን፡፡ ሰው ከመሆንህ በፊት መምህር አትሁን፡፡ ሰው ከመሆንህ በፊት ፖለቲከኛ አትሁን፡፡ ሰው ከመሆንህ በፊት ጋዜጠኛ አትሁን፡፡ ሰው ከመሆንህ በፊት መሪ፣ መካሪ፣ አውሪ፣ ዘማሪ፣ ጸሐፊ፣ ለጣፊ፣ ሰባኪ፣ ሹመኛ፣ ወገኛ.... ሌላም አትሁን፡፡

ዓለም፣ ኢትዮጵያም ያጣችው ይህንን ሁሉ አይደለም፡፡ ሰው የሚሆንላትን እንጂ፡፡ ይልቁንስ ከሁሉ በፊት ሰው ሁን፡፡ ሰው መሆን ከእነዚህ ሁሉ የተሻለ ማንነት ነውና፡፡

"ሰብአዊነት የጎደለው ሙያ በመርዝ ዕቃ ላይ እንደተቀመጠ ጣፋጭ ምግብ ነው" ይላሉ አበው፡፡ የችግሮቻችን ሁሉ መነሻም ሰብአዊነት የጎደለው ግብራችን ነው፡፡
#ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ
@UoG_Psych
525 views07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 12:10:27 #የህፃናት_ስብእና

ህፃን ዳክዬዎች ከተፈለፈሉ በሁለተኛው ቀን ይዋኛሉ። ህፃን የተራራ ፍየሎች በተወለዱ ቀን መራመድ ይችላሉ። ህፃን ልጆች ግን ሲወለዱ ምንም ማድረግ ስለማይችሉ ሙሉ በሙሉ በወላጆች ላይ ጥገኛ ናቸው። ከወላጆች ጋር ያለቸው ግንኙነት ስብእናቸው ላይ ትልቅ ተፅእኖ ስለሚኖረው አንዳንድ ጊዜ አእምሯቸው ከነጭ ወረቀት ጋር ይመሳሰላል።

ሁለት ልጅ ያላቸው ወላጆች ህፃናት ነጭ ወረቀት እንዳልሆኑ ምስክር ናቸው። ገና እንተወለዱ አንዳንዶቹ ተጫዋች ናቸው፤ ሌሎቹ ዝምተኛ። አንዳንዶቹ ሲያባብሏቸው ዝም ይላሉ ሌሎቹ እልኸኛ ናቸው። በተጨማሪም አንዳንድ ልጆች ጥሩ ቤተሰብና አካባቢ አድገው ስነልቦናዊ ችግሮች ያጋጥማቸዋል። አንዳንድ ልጆች አስቸጋሪ ቤተሰብ ውስጥ አድገው የስነልቦና ችግር አያግጥማቸውም።

ምክኒያቱ ህፃናት የራሳቸው ስብእና ስላላቸው ነው። የልጆች አስተዳደግን በተመለከተ የህፃናትን ስሜት ፍላጎት ግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው። የ3 ወር ልጅ የራሱ ስብእና ስሜት አለው። የ3 ወር ልጅ ሲዳስሱት ፍቅር ይሰማዋል፤ ከፍተኛ ጩኸት ሲሰማ ይፈራል፤ እንዳይንቀሳቀስ ሲደረግ ይናደዳል...ወዘተ

እያንዳንዱ ህፃን የተለየ ነው። ልዩ ስብእናቸውን በመረዳት ትኩረት እና እንክብካቤ መስጠት በራሳቸው የሚተማመኑ ደስተኛ ሰዎች እንዲሆኑ ለማድረግ ያግዛል።

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!!!
ከዶ/ር ዮናስ ላቀው
@UoG_Psych
781 views09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 09:59:13 #እንዳይፈረድብህ_በባልንጀራህ_ላይ_አትፍረድ

በአንድ ወቅት በግብጽ ገዳማት አንድ ወጣኒ መነኩሴ “ጥፋት አጠፋ፣ ሥርዓተ ገዳም አፋለሰ” ተብሎ መናንያኑ ጉዳዩን እንዲያዩና እንዲወስኑበት ከየበአታቸው ተጠሩ፡፡ ከተጠሩት መነኮሳት መካከል አንዱ ጥቁሩ ኢትዮጵያዊው ሙሴ ጸሊም ነበር፡፡ እርሱም ሁሉም ከተሰበሰቡ በኋላ ዘግይቶ በተቀደደ አቁማዳ አሸዋ በጀርባው አዝሎ አሸዋውን ከኋላው እያፈሰሰ መጥቶ በመሃላቸው ተገኘ፡፡

የተሰበሰቡት መነኮሳትም አባ ሙሴን ይህን ስለምን አደረግከው ብለው በጠየቁት ጊዜ በሀዘን ተውጦ “በጀርባዬ የማላያቸውን ስፍር ቁጥር የሌላቸው ኃጢአቶቼን ተሸክሜ ሳለሁ በወንድሜ ለመፍረድ መጥቻለሁ” አላቸው፡፡ መነኮሳቱም እጅግ ተጸጸቱ፡፡ ጉባኤውም ፍርዱን ትቶ ተበተነ፡፡

“እንዳይፈረድብህ በባልንጀራህ አትፍረድ” የሚለውን የወንጌል ቃልም በተግባር አስተማራቸው፡፡ ልብን በሚነካ በዚህ በጎ ትምህርቱም መነኮሳቱን ከመፍረድ ሃጢአት ታደጋቸው፡፡
@UoG_Psych
743 views06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 13:51:13 #የአእምሮ_ሞት_እና_የማፈን_ምርመራ
#Brain_death_and_apnea_test

አንድ ሰው ፅኑ ህክምና ክፍል (ICU) ሲታከም ከፍተኛ ክትትል ይደረግለታል በተጨማሪም የሰውነቱ ክፍሎች መስራት የሚገባቸውን ስራ የሚተኩ ማሽኖች ሊኖሩ ይችላሉ።

አንድ ሰው አእምሮው ሙሉለሙሉ ሞቶ ነፍሱ ግን ላትወጣ ትችላለች። ሳንባውን አእምሮው ማዘዝ ሲያቆም በማሺን እንዲተነፍስ (Mechanical ventilation) ማድረግ ይቻላል። ልብ ያለ አእምሮ ትእዛዝ መምታት ትችላለች። ስለዚህ ግለሰቡ ልቡ ይመታል፤ ይተነፍሳል ግን አእምሮው ሞቷል። መስተካከል የሚችል ህመም ሳይኖር የአእምሮ ሞት ላይ ከደረሰ በህክምናው እንደሞት ስለሚቆጠር የመተንፈሻ ማሽኑ ሌላ የሚተርፍ ታካሚ እንዲጠቀምበት ይነቀላል። (መስተካከል የሚችል ማንኛውም አይነት ነገር ከመሞከር ግን ወደ ኋላ አይባልም።)

ውሳኔው እጅግ ትልቅ ውሳኔ ስለሆነ አእምሮው መሞቱን በሚገባ ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ስለዚህ የአእምሮ ሞትን ቢያንስ በሁለት የተለያዩ ሀኪሞች ለየብቻ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው። በተጨማሪም የሚያስፈራ ምርመራ አለው። የማፈን ምርመራ (Apnea test)።

የትንፋሽ ምርመራውን ለመስራት በቅድሚያ 100% ኦክስጅን በደንብ ለታካሚው በማሽኑ አማካኝነት ይሰጠዋል። ከዛ ማሽኑ ይነቀላል። ግለሰቡ ምንም የመተንፈስ ምልክት ሳያሳይ ለ6-8 ደቂቃዎች ከቆየ በደሙ ውስጥ ያለው የካርቦን ዳይኦክሳይድ ይለካል። ከ60mm Hg በላይ ከሆነ አእምሮው ሞቷል ማለት ነው። አንድ ሰው ትንፋሽን የሚቆጣጠረው ወሳኝ የአእምሮ ክፍል ሳይሞት ቢፈልግ እንኳን ትንፋሹን መያዝ አይችልም። የካርቦን ዳይ ኦክሳይድ መጠን ከፍ ሲል ሳይወድ በግድ አእምሮው ያስተነፍሰዋል። ይህን ካላደረገ አእምሮው መሞቱን ማረጋገጥ ይቻላል።

ህክምና ከባድ ስራ ነው። አንዳንዴ እጅግ አስቸጋሪ ውሳኔዎች መወሰን ይጠይቃል። ብዙ ሰው ስለሞት ማውራትም ማሰብም አይፈልግም። በከፍተኛ ጫና ውስጥ በፅኑ ህክምና ክፍል ውስጥ በየደቂቃው ከሞት ጋር ግብግብ ገጥማችሁ ለምትሰሩ ነርሶች፣ የአንስቴዢያ፣ የልብ የሳንባ እና የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሀኪሞች ጭንቀታችሁን እንረዳለን። ስለ አገልግሎታችሁ እናመሰግናለን።

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!!
ከዶ/ር ዮናስ ላቀው
@UoG_Psych
766 views10:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 21:31:03 #ከአእምሮ_ህክምና_ጋር_የተያያዙ_ትክክል_ያልሆኑ_ግምቶች

ታካሚዎች የውስጥ ደዌ ወይም የቀዶ ጥገና ሀኪም ጋር ሲሄዱ ከሞላ ጎደል ምን መጠበቅ እንዳለባቸው ያውቃሉ፡፡ የአእምሮ ሀኪም ጋር ሲኬድ ምንድነው የሚያጋጥመው? ምን እንደሚጠብቁ ስለማያውቁ ለመሄድ ያመነታሉ፡፡ ከአእምሮ ህክምና ጋር ተያይዞ የሚነሱ የተሳሳቱ ግምቶች፦

• የአእምሮ ህክምና ራሱን ለማያውቅ ሰው ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎች በጓደኞቻቸው፣ በቤተሰብ ወይም በሀኪም የአእምሮ ህክምና እንዲያደርጉ ሲመከሩ ደስተኛ አይሆኑም፡፡ "እኔ ራሴን አውቃለሁ፡፡" ይላሉ፡፡ ከባድ የአእምሮ መረበሽ ያለባቸው ሰዎች ህክምና ያስፈልጋቸዋል፡፡ ነገር ግን የአእምሮ ህክምና ከሚያስፈልጋቸው ሰዎች አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት የስራ ጫና ያለባቸው፣ የልጅ አስተዳደግ የሚያስጨንቃቸው፣ ትዳራቸው/የፍቅር ህይወታቸው የሚያሳስባቸው...ወዘተ ናቸው፡፡

• የአእምሮ ሀኪሞች አእምሮ ያነብባሉ፡፡

የአእምሮ ሀኪም አእምሮ የሚያነብ የሚመስላቸው ሰዎች አሉ፡፡ "ይሀው መጥቻለው አንብቡና መድሀኒት ስጡኝ" አይነት አቋም ይዘዉ የሚመጡ ፡፡ የዚህ አይነት ግምት ምንጩ ባህላዊና ሀይማኖታዊ ህክምናዎች ናቸው፡፡ አእምሮ አናነብም!! ታካሚን ለመረዳትና ለመርዳት የሚሰማውንና የሚያስበውን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ብዙ ጥያቄዎች ልንጠይቅ እንችላለን ሆኖም ታካሚዎች ምቾት የማይሰጣቸው ከሆነ ያለመመለስ ፍላጎታቸውን እናከብራለን፡፡ በተጨማሪም ራስን ወይም ሌላን ሰው ስለመጉዳት ካልሆነ በቀር የምንነጋገራቸው ነገሮች በሀኪም እና በታካሚ መሀከል የሚጠበቅ ሚስጥር ነው፡፡

• የኔን አይነት ነገርማ ተሰምቶ አይታወቅም፡፡

አንዳንድ ሰዎች ያጋጠማቸው ሁኔታ ወይም የሚያስቡት ሀሳብ የሚከብድ ነው ብለው ሲገምቱ ተረካቸውን ለማስተካከል ይሞክራሉ፡፡ ሁሉም ሰው የየራሱ ታሪክ ቢኖረውም ተመሳሳይ ነገር ውስጥ ያለፉ ሰዎች ታሪክ ከመፅሀፍት ወይም በስራቸን ያጋጥመናል፡፡የምንሰማው ነገር ለመጀመሪያ ጊዜ የምንሰማው አይሆንም፡፡ ሰዎች ስለ አእምሮ ህመምም ሆነ ስለህክምናው መድልዖ እና መገለልን በመፍራት እርስበርስ አያወሩም፡፡ ስለዚህ ሁሉም ከአለም ተነጥሎ ብቻውን አየታመመ ያለ ይመስለዋል፡፡

በአጠቃላይ አብዛኞቹ የአእምሮ ህመሞች ሰዎች በጊዜ ህክምና ካገኙ ጥሩ ውጤት ይኖራቸዋል፡፡

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!!!
ከዶ/ር ዮናስ ላቀው
@UoG_Psych
624 views18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 10:10:53 አንድ መምህር በሚያስተምርበት ክፍል ውስጥ በርካታ ፊኛዎችን በማምጣት ተማሪዎች ፊኛዎቹን እንዲነፏቸውና በእያንዳንዳቸው ላይ ስማቸውን እንዲጽፉባቸው አደረገ፡፡ ከዚያም መምህሩ ፊኛዎቹን ከቀላቀላቸው በኋላ ክፍሉ ውስጥ ለቀቃቸው፡፡ መምህሩም ለተማሪዎቹ "በአምስት ደቂቃ ውስጥ ስማችሁ የተጻፈበትን ፊኛ ፈልጋችሁ አግኙ" በማለት ትዕዛዝ ሰጣቸው፡፡
ተማሪዎቹም በታዘዙት መሰረት ስማቸውን ለመግኘት ተሯሯጡ፣ ተጣደፉ፡፡ ነገር ግን አንዳቸውም ስማቸውን ሳያገኙ የተሰጣቸው ደቂቃ አለቀ፡፡ ከዚያም መምህሩ ወደ ፊኛዎቹ እንዲጠጉ ተማሪዎቹን ካዘዛቸው በኋላ አጠገባቸው ያገኙት ፊኛ ላይ የተጻፈውን ስም አይተው ስሙ ለተጻፈው ተማሪ እንዲሰጡ ነገራቸው፡፡ በዚህም ሁለት ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሁሉም ተማሪዎች ስማቸው የተጻፈበትን ፊኛ አገኙ፡፡
በመጨረሻም መምህሩ እንዲህ አላቸው "ፊኛዎች ልክ እንደ ደስታ ናቸው፡፡ማንም የራሱን ብቻ ስለፈለገ አያገኝም፡፡ በአንጻሩ እያንዳንዱ ለሌላው ቢገደው፣ ሁሉም የየራሱን በፍጥነት ማግኘት ይችላል፡፡"
@UoG_Psych
580 views07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 08:44:51 #የቋንቋ_እና_የንግግር_እድገት_እክል #Language_and_Speech_Disorders_or_delay

ቋንቋ ማለት ሰዎች በሚኖሩበት ማህበረሰብ ከሌሎች ጋር ለመግባባት
የሚጠቀሟቸው ድምፆች፣ ቃላት፣ ምልክቶች፣ ንግግር እና ፅሁፍን ያካትታል።
Language Delay/Disorder
የቋንቋ እክል አለ የምንለው አንድ ልጅ ሀሳቡን በንግግር መግለፅ ሲቸገር ወይም ሌሎች
የሚሉትን ሀሳብ ለመረዳት ሲቸገር እና በተጨማሪም ለመናገር መዘግየት (በእድሜው በሚጠበቀው ልክ መናገር ቃላት ማውጣት ሳይችል ሲቀር)
ውስን ቃላት ብቻ መናገር ሰው የሚለውን ብቻ መድገም ሁለት ቃላትን አጣምሮ ሀሳብን መግለፅ አለመቻል
አረፍተ ነገር መመሥረት አለመቻል
የቃላትን ትርጉም አለመረዳት
ሀሳብን በንግግርም ይሁን በፅሁፍ ለመግለፅ መቸገር እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
የቋንቋ መዘግየት ምክንያቶች
ከቤተሰብ የዘር ውርስ ለንግግር የማያበረታቱ አካባቢያዊ ሁኔታዎች(TV እና መሠል ከሰው ጋር መነጋገር የሚገድቡ ነገሮች ማዘውተር)
የንግግር እድገት እክል መኖር
ኦቲዝም መኖር የአእምሮ እድገት ውስንነት መኖር
የዳወን ሲንድሮም መኖር እና ልሎች የእድገት እክሎች ሲኖሩ
ከየእድሜው የሚጠበቁ የቃላት ብዛት
በ1 አመት :- ከ20 -50 ቃላት
በ2አመት:-200 -300 ቃላት እና ሁለት ቃላት በማጣመር መናገር
3አመት ላይ ከልጅ ልጅ ይለያያል:- ከ350- 900 ቃላት
በእነዚህ አመታት አንድ ልጅ ምንም የማያወራ ከሆነ የመስማት ሁኔታውን
ማስመርመር ማረጋገጥ በጣም አስፈላጊ ነው።
ንግግር ማለት ቋንቋን ለመፍጠር የሚያግዙ የነርቭ እና የጡንቻ ስርአቶችን
በመጠቀም እና በማቀናጀት ተገቢውን ድምፅ ማውጣት መቻል ማለት ነው።
Speech Delay/Disorder
የንግግር እክል አለ የምንለው ልጁ ያወራል/የሚለው ነገር አለ ነገር ግን ሌሎች እሱ የሚለውን በቀላሉ መረዳት ሲቸገሩ ማለትም ድምፅን በአግባቡ የማውጣት ችግር ሲኖር
መኮላተፍ ሲኖር
አንድን ቃል በሌላ ቃል ሲል ለምሳሌ: 'ሰው' ለማለት 'ተው' ሲል ፣ 'በላ'
ለማለት 'ፈላ' የመሳሰሉት ሲል
የንግግር እክል ምክንያቶችም
የምላስ፣ ትናጋና ከንፈር የማቀናጀት እክል ሲኖር በህፃናት ላይም ይሁን በአዋቂዎች ላይ የአእምሮ ጉዳት ሲኖር ነው፡፡
@UoG_Psych
638 views05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 07:50:27 በአንድ ወቅት የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛ ንጉሱን እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል....
“ለመሆኑ ...ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? ”
ጃንሆይም ቆፍጠን ባለ አነጋገር ለዛ...
“ኢትዮጵያዊነት ኩራትና ትህትና ነው” አሉት።
ጋዜጠኛውም ቢሆን የዋዛ አልነበረምና......
“ይቅርታ ያድርጉልኝና ጃንሆይ ይሄ ኩራት እና ትህትና የሚሉት ነገር እርስ
በርሱ የሚጣረስ ማንነት አይመስልዎትም?” የሚል ጥያቄ ያስከትላል።
ንጉሱም እንዲህ አሉ .....“አየህ አንድ በጣም ተራ የምትለው ገበሬ ቤት በእንግድነት
ብትሄድ ያለውን አብልቶ፤ እግርህን አጥቦ፤ ያጠበውን እግርህን ስሞ፤ አልጋውን ላንተ
ለቆ እርሱ ግን መሬት ላይ ይተኛል። በዚያው ልክ በሚስቱ፣ በርስቱና በሃገሩ ላይ
ብትመጣበት ደግሞ በግንባርህ ላይ ጥይት ይቆጥርልሃል፤ ስለዚህ አይጋጭም፤ ነገር
ግን ይሄንን ነገር ለመረዳት አንተ ራስህ ኢትዮጵያዊ መሆን አለብህ” ነበር ያሉት።
@UoG_Psych
654 views04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 14:00:06 #የእህትማማች_ፉክክር

ታሀኒ አልጀሚል ቆንጅዬ፣ ዘናጭ፣ ኦክስፎርድ የተማረች ወጣት ናት። በሰዎች አይን ስትታይ ምንም የሚጎድላት ነገር የለም። በመልካም ተግባርም አትታማም። 6ቢሊዮን ዳላር (በፊት ዶላር ነበር የምለው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቢጤ ግፊት ምክኒያት ነው ዳላር ማለት የጀመርኩት ) አሰባስባለች። ነገር ግን በስራዋም ሆነ ህይወቷ ደስተኛ አይደለችም። በሌሎች አይን እንደ ተአምር የሚታዩት ስኬቶች በራሷ አይን ግን ምንም ናቸው።

ምክኒያቱ ደግሞ ከእህቷ ጋር ከህፃንነት ጀምሮ የነበረ ፉክክር ነው። ወላጆቿ እህቷ ካሚላን የበለጠ ስለሚወዱ ታሀኒ ምንም ብትሰራ ያጣጥላሉ። "እንደ እህትሽ አትሆኚም?!" ይሉዋታል እንጂ የሰራችውን ወይም ያሳካችውን አያደንቁላትም።

በእህትማማቾች ወይም በወንድማማቾች መካከል ፉክክር የተለመደ ነው። ነገር ግን ወላጆች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። በልጅነት አእምሮ የሚቀፁ ነገሮች ወደፊት ብዙ ተፅእኖ ያሳድራሉ። አንዳንድ ጊዜ ወላጆች ለአንዱ ልጃቸው ሊያግዙ ይችላሉ። እንዲታገዝላቸው የሚፈልጉ ልጆች ደግሞ እራሳቸው ነገር ፈልገው እራሳቸው እንደተጎዳ ሆነው ወንድም ወይም እህታቸውን ለማስቆጣት ወይም ለማስገረፍ ሊሄዱ ይችላሉ። እነዚህን ግጭቶች ወላጆች በብልሀት መያዝ ይጠበቅባቸዋል።

የእህትማማች (የወንድማማች) ፉክክር ጤነኛ ሲሆን እንደ ሴሪና ዊሊያምስና እንደቬነስ ዊሊያምስ ለስኬት ያግዛል። እንደ አቤልና ቃየል ሲሆን ደግሞ ብዙ መዘዝ ያስከትላል።

ታሀኒ አልጀሚል The Good Place የተባለው አስቂኝ ድራማ ላይ ያለች ገፀ ባህሪ ናት። ወጣ ያለ አስቂኝ ድራማ የምትወዱ ከሆነ ለመዝናናትም ለማውጠንጠንም The Good Place የተመቸ ነው።

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ከዶ/ር ዮናስ ላቀው
@UoG_Psych
659 views11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ