Get Mystery Box with random crypto!

አንድ አባት ነበር 4 ልጆች ነበሩት እናም ከአንድ ነገር ሊያሰተምራቸው ሰለ ፈለገ አራቱንም ልጆች | ቱንቢ ላቭ ሚዲያ 💟

አንድ አባት ነበር 4 ልጆች ነበሩት እናም ከአንድ ነገር ሊያሰተምራቸው ሰለ ፈለገ አራቱንም ልጆች በተለያየ የአየር ፀባይ ውቅት ወደ አንድ ሾላ ዛፍ ላካቸው።
የመጀመሪያውን ልጅ በክረምት ላከው፣ ልጅየውም ወደ አባቱ ተመልሶ አባቴ የላከኝ ዛፍ ምንም እኮ ፍሬ የለውም በቃ አረንጓዴ ቅጥል ስላለው ለጥላ ሊሆን ይችላል።
ሁለተኛውን እንዲሁ በፀደይ ወቅት ወደዚሁ ሾላ ዛፍ ይልከዋል ፣ ልጁም የሾላ ፍሬ ይዞለት በመምጣት ለአባቱ ምላሹን ሰጠ፣ ዛፉ ፍሬ አለው ደግሞም ለጥላ ምቹ ነው አለው።
ሶሰተኛውን ልጅ ደግሞ በበጋ ወደዚሁ ዛፍ ላከው ፣ ልጅም ሲመለስ አባቢ ዛፋ እኮ ፍሬ የለውም ቅጠሉም እየደረቀ ነው መሰለኝ ጠውልጓል አለው።
አራተኛውን ልጅ በበልግ ውቅት ላከው ልጁ ከሾላ ዛፍ ሲመልስ  እንዲ አለ ፣ አባቢ ምን ብታስብ ነው እንኳን ፍሬ ቅጠል ወደሌለው ወደ ደረቀ ዛፍ የላከኝ? አዎ አባቢ በቃ ማለት የምችለው ነገር ዛፋ ለምንም አይጠቅምም ነው አለ።
አባታቸው አንደ ቀን ምሽት አራቱንም ልጆች ሰብስቦ እንዲ ብሎ አስተማራቸው ልጆቼ ሆይ  እኔ የላክዋችሁ ዛፍ 1 የሾላ ዛፍ ጋ ነበር ፣ ነገር ግን በተለያየ ወቅት ሰለሄዳችሁ የተለያየ መልስ ይዛችሁ መጣቹ። አያችሁ ችግሩ የዛፋ ሳይሆን የሄዳችሁበት የወቅትና ጊዜ ስለተለያየ ነው ፣ ስላላወቃችሁ ነው።

      እናም ልጆቼ ሆይ ማንም ሰው ስትቀርቡና ስትተዋወቁ ያንን ሰው ባገኛችሁት የጊዜ ወቅት አትፍረዱት ፣ ያን ሰው ለማወቅና ማን እንደሆነ ለመናገር ፍላጎቱና ሃሳቡ ካላችሁ አብራችሁ ጊዜ አሳልፋ። በአንደ ሁኔታና በአንድ አጋጣሚ የሰው ማንነት አይወሰንም። ልጆቼ ሆይ አደራ የሚል የአባትነትን ምክር ለህይወት ዘመናቸው ስንቅ አድርጎ ሰጣቸው።