Get Mystery Box with random crypto!

‍ ይድረስ ኢንተርኔት ለምትጠቀሙ እህቶች በኢንተርኔት ከንቱ ምኞት ትዳርዋን የተበላሸባት፤ | ጡባ ሊል ጉረባእ የሰለፍዮች መድረሳ ቻናል

ይድረስ
ኢንተርኔት ለምትጠቀሙ እህቶች

በኢንተርኔት ከንቱ ምኞት ትዳርዋን የተበላሸባት፤ ህይወቷን የጨለመባት እንስት አስተማሪ ታሪክ…

ወጉ ወዲህ ነው
ሚስት አላህ ይጠብቀንና በኢንተርኔት ሱስ የተጠመደች ናት። ባለቤትዋ ከዚህ ተግባርዋ እንድትቆጠብ በተደጋጋሚ ቢመክራትም ልትቀበለው አልቻለችም። ብዙ ለመናት ብዙ አስመከራት "አሻፈረኝ" አለች። የምትጠቀምበትን ስልክ ሳይቀር ወስዶባታል። እሷም ሌላ ስልክ በመፈለግ ኢንተርኔት ላይ መዘውተሯን ቀጠለች።

በዚህ ጊዜ ባል አንድ ዘዴ ይዘይዳል
ወደ facebook በመግባት እንደ ሚባለው "fake acount" (የውሸት አድራሻ) በመክፈት ስሙን ይቀይርና ፕሮፋይሉ ላይ ሀብታምና ቆንጆ የሚመስል የወንድ ምስል ያስቀምጣል። ከዝያ በኋላ የሚስቱን የ facebook አድራሻ በመፈለግ ያናግራት ጀመረ።

ጨዋታው የተጀመረው እዚህ ቦታ ነበር
በሰላምታ የተጀመረው ንግግር ወደ ትውውቅ ይሸጋገርና ያለችበትን የኑሮ ሁኔታ ጨርሳ ትነግረዋለች። እሱ ግን እየዋሻት እሷን በምትፈልገው አይነት ራሱን እየገለፀ ያጫውታታል።
ባለ ትዳር እንደሆነችና ነገር ግን በትዳሯ ላይ ደስተኛ እንዳልሆነች ስትነግረው
"እንግዲያውስ ባልሽን ይፍታሽና ከእኔጋ እንደመር" ይላታል።
ባቀረበላት ሀሳብ ደስተኛ ሆና ከባልዋ ጋ በምን ዓይነት መልኩ መፋታት እንዳለባት መላ ይፈልጋሉ። እሱም "በቃ ሳትጎዳዱና ሳትጨቃጨቁ እንድትለያዩ ችግር በማይፈጥር መልኩ ባህሪሽን ቀይሪበት" ይላታል።

ባል ስራ ውሎ ማታ ሲገባ የሚስቱ ባህሪይ ከቀን ወደ ቀን እየተቀያየረ ይመጣል። ሚስት የማታውቀው ባል የፈጠረው ጨዋታ ነውና ቀን እያወራት ማታ ገብቶ ይታዘባታል። [አላህ ይጠብቀን]

ጨዋታው ሲጧጧፍ ባል ማታ ይገባና
"ሰሞኑ እያየሁብሽ ያለው ነገር እያስደሰተኝ አይደለም ምን ተፈጥሮ ነው?" ይላታል
"ምንም" ትለዋለች
"ንገሪኝ ችግርሽ ዝምታ መፍትሄ አይሆንም" ሲላት
"ምንም አልሆንኩም" ትለዋለች
"ሀሳብሽ በግልፅ ንገሪኝ ከእኔ መለየት ትፈልጊያለሽ ያልተመቸሽ ነገር አለ እንዴ?" ሲላት
"ቢሆን አይከፋኝም" ብላ ፍላጎትዋን ገለፀችለት።

ፍላጎቷን ግልፅ ካደረገች በኋላ ባልየው ቀጥታ ወደ ፈለገው ጨዋታ ይገባና ያናግራታል
"እንግዲህ መለያየታችን አይቀሬ ከሆነ አንቺም የሄድሽበት እንዲቀናሽ እኔም ቤቴና ንብረቴ ተበታትኖ ህይወቴ እንዳይበላሽ ከመሄድሽ በፊት ሁለተኛ ላግባና ልክ እንዳገባኋት ለእሷ አስረክበሽ ትሄጃለሽ" ይላታል።
  ሚስትም ያሳሰባት ሁለተኛ ማግባቱ አለ ማግባቱ ሳይሆን የእሷ መፈታት ነበርና "ምንም ችግር የለውም" ብላ ትስማማለች።

ባልየው በማግስቱ ወደ ሚስቱ ቤተሰቦች በመሄድ የተነጋገሩበት ነገር ያጫውታቸውና ሁለተኛ ሊያገባ መሆኑ ይነግራቸዋል።
ሁለተኛ ሚስት ፍለጋ ተ ጀ መ ረ

ባል ሊያገባት ሚስት ደግሞ አስረክባት የምትወጣዋ ሁለተኛ ሚስት በሁለቱም ብርቱ ፍለጋ "ትሆናለች፣ ትመጥናለች" የተባለችዋን አፈላልገው አገኙ።
ያዝ እንግዲህ……

የሁለተኛዋ ሚስት የኒካህ ቀጠሮ ይያዛል። ልብ በሉ ሁለተኛዋ እንደ መጣች የመጀመሪያዋ ተሸኝታ ያ በኢንተርኔት መንፈስ ብቻ የምታውቀው ባልዋ ሊያገባት ነው።

የማይደርስ የለምና የኒካሁ ቀን ደረሰ። ባል ልክ የሁለተኛ ሚስቱ ኒካህ እንዳሰረ ያ ሚስቱን ሌላ ሰው መስሎ ያወራበት የነበረው የ facebook አድራሻ ዘግቶት ከኢንተርኔት መንደር ይወጣል።
لا إله إلا الله

የመጀመሪያዋ ሚስት ባልዋ ሌላ እንዳገባና ከባልዋ ተለያይታ አዲስ የተዋወቀችው ሰወዬ ልታገባው እንደሆነ ልታበስረው ስትገባ ያ በውሸት ሲያወራት የነበረው ባለ facebook አድራሻው ዘግቶ ከመንደሩ ጠፍቷል።

ዱንያ የት አትጥበባት?
"ምድር ዋጭኝ" ብትላት መች ልትውጣት? ህይወት ጨልሞባት፣ መኖር አስጠልቷት ራሷን እየረገመች አዝና ተክዛ ቁጭ ብላለች።

ባል አዲሷ ሙሽራው ጋ መቆየት ያለበትን ቆይቶ መጫወት ያለበትን ተጫውቶ ወደ ቀድሞ ሚስቱ ቤት ሲሄድ በሀዘን ተውጣ ተቀምጣለች።
"ምንድን ነው ሰላም አይደል እንዴ?" ሲላት
"ሰላም ነው" ትለዋለች
"ምን ሆንሽ?"  "ምንም"
ትቷት ይሄዳል።

አሁንም ተመልሶ ሲመጣ ሰውነቷ ከሳስቶ ፊቷ ተሸብሽቦ ያገኛታል
"ምንድን ነው የሆንሽው?"
"ምንም አልሆንኩም"
"ያስቀየምኩሽ ነገር አለ"
"ኧረ የለም"
"ሀሳብ መቀየር አስበሽ ነው?"
ፀጥ ረጭ አለች።

የዛኔ ባል አጠገቧ ቁጭ ብሎ እያፅናናት
"ምን ላርግ ታድያ? ከአንቺ መኖር እየፈለግሁ፣ ሳልጠላሽ፣ ሳላስከፋሽ በራስሽ ፍላጎት ያመጣሽው ሀሳብ ነው። እኔ ግን አሁንም ቢሆን የማከብርሽ የምወድሽ ባለቤቴ ነሽ። አንቺም ከእኔ የመለየት ፍላጎት ከሌለሽ ያመጣኋትም ሙስሊም እህትሽ ናት አብራችሁ ትኖራላችሁ። እሷም በቤቷ አንቺም በቤትሽ አብረን እንኑር።" አላት

በዚህ ሰዓት ካላይዋ ላይ የተጫናት ተራራ የተነሳላት በሚመስል መልኩ በደስታ ፈንጥዛ ባልዋን እየሳመችና እያመሰገነች እያለቀሰች ደስተኝነቷን ገለፀችለት።

በመጨረሻም ባልየው ባለ ሁለት ሲም ሆኖ ከሁለቱም ሚስቶቹ ጋ አብረው መኖር ጀመሩ።


NB: ታሪኩ ላይ የተጠቀሱ በሸሪዓ ክልከላ ያለባቸው ነጥቦች አሉ [ፎቶ መጠቀምና ውሸትን] ይመስል
ዘንግተናቸው ሳይሆን ከታሪኩ ብዙ ሰው ሊማር ይችላል ብለን ስላሰብን ነው።
ማስተላለፍ የተፈለገውም ባሎች እንዲህ እንዲያደርጉ ሳይሆን ሴቶች ከምንም ነገር በፊት ክብራቸውን (ትዳራቸውን) ማክበርና መታዘዝ እንዳለባቸው ለማስገንዘብ ነው።

ኮፒ!!

በጣም ገራሚ ትምህርት አለው አንብቡት በተለይ ሴቶች ወንዶችም እንደዛው።
https://t.me/tubaliligurebae/11431
https://t.me/tubaliligurebae/11431