Get Mystery Box with random crypto!

ጧሊበል ኢልም Tube (طالب العلم)

የቴሌግራም ቻናል አርማ tualibelilm — ጧሊበል ኢልም Tube (طالب العلم)
የቴሌግራም ቻናል አርማ tualibelilm — ጧሊበል ኢልም Tube (طالب العلم)
የሰርጥ አድራሻ: @tualibelilm
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.21K
የሰርጥ መግለጫ

በቻናላችን የሚለቀቁ ፕሮግራሞች
💎ሰፊና ተከታታይ ደርስ በፅሁፍ እና በፎቶ
💎ሀዲሶች
💎የነብያት ታሪክ
💎ሌሎችም
https://t.me/joinchat/i_MVpiNc5NtjMjE0
የyoutube ቻናላችን ሰብስክራይብ ያድርጉ።
https://youtube.com/channel/UCNgJGsz89v7K6HmuT2AgVSg
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥያቄ
@ilmfelagi1

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-16 17:54:25 እውነተኛ ፍቅር

ክፍል

ከሻም ጉዞ መልስ ከድጃ (ረዐ) ለሙሀመድ (ሰዐወ) "ለአንተ እኔ ዘንድ ጥሩ ደስታና ስጦታ ተቀምጦልሀል ከሁሉም ሰራተኞች የበለጠ እጥፍ ተጨማሪ ገንዘብ ይከፈልሀል" አለችው፡፡ ሙሀመድም (ሰዐወ) ከጉዞ መልስ አጎቱ ጋር ተመለሰ፡፡ አቡጣሊብም አባት ለልጅ አቀባበል ከሚያደርገው በላይ በደስታ ተቀበሉት፡፡ ከዚያም እንዲህ አሉት
"ልጄ ሆይ ከድጃ ከፈለችህ"
ሙሀመድም "ከውሉ በተጨማሪ ትርፍ ገንዘብ ጨምራ እንደምትሰጠኝ ቃል ገባችልኝ " አለ
አቡጣሊብም "ልጄ ሆይ የወላጆችህ አደራ አለብኝ እንደምታዬኝ አርጅቻለሁ የሞትም ምልክቱ እየታየብኝ ነው ስለዚህ አንተን ድሬ ወግ ማዕረግህን ማየት እፈልጋለሁኝ እናም ከቁረይሾች ጥሩ ሚስት ብፈልግልህና ብድርህስ " አሉ፡፡
ሙሀመድም "አጎቴ ሆይ አንተ እንደፈለክ ማድረግ ትችላለህ እኔ ያንተን ትዕዛዝ ለመፈፀም ዝግጁ ነኝ " አለ፡፡
ከሻም መልስ በሁለተኛው ቀን ታላቁ ሙሀመድ (ሰዐወ) ገላቸውን ታጥበው አቡጣሊብ በገዙላቸው ልብስ ተውበው ወደ ከድጃ ሄዱ፡፡ ከድጃም እውነተኛ ፣ ታማኝ ፣ ፍትሀዊ ፣ አዛኝ ፣ መልካም ሰሪን ታላቁን ወጣት በውበቱ ላይ አዲስ ልብስን ተጎናፅፎ ስታየው ተደነቀች ከዚያም "እንዲህ አምረህ የመጣኸው ከኔ አንድ ነገር ፈልገህ ሳይሆን አይቀርም ምን ልታዘዝ ሀጃህ ምንድነው?" አለችው፡፡
"ከአንቺ ዘንድ ያለኝን ገንዘብ ፈልጌ ነው " አላት፡፡
"መሀመድ ሆይ ይህ ውዐትና ገንዘብ ይዘህ በንደዚህ ሁኔታህ ምን ልትሰራበት ነው" አለችው፡፡
"አጎቴ ከቁረይሽ የሆነችን ሚስት እድርልሀለው ስላለኝ ተስማምቼ ነው የመጣሁት " አላት፡፡
"ሚስት ልታገባ አስበህ ከሆነ እኔ እጅግ ቆንጆ የሆነች ገንዘብ ያላት ለዘርህ ቅርብ የሆነች ሹማምንቶች ለጋብቻ ጠይቀዋት እንቢ ያለች በሰዎች ዘንድ የተከበረች አዕምሮዋ የተረጋጋና የሞላ አንተን እንጂ ከአንተ ምንም የማትፈልግ ሚስት አዘጋጅቼልሀለው፡፡" አለችና እንዲህ ስትል ቀጠለች "ከአንተ የማልደብቀው ሁለት ነውር አላት አንደኛው ነውሯ አግብታ ታውቃለች ሁለተኛው በዕድሜ ከአንተ ትበልጣለች " አለች፡፡
መሀመድም "አንቺ ጥሩዋ ሴት ሆይ ማናት እሷ የትስ ነው ያለችው " አላት
"ያንተ ምርኮኛ ናት እዚሁ ቅርብ አጠገብህ ታያታለህ ስሟም ከድጃ ይባላል" አለችው፡፡

መሀመድም ሁሉም ነገር በተገለጠለት ጊዜ ምንም መልስ ሳይሰጥ ዝም አለ፡፡
ከድጃም "የእሺታ መልስ ስጠኝና ልቤን አሳርፈው" አለችው፡፡
አሁንም ከወጣቱ መልስ ስታጣ "አላህ ካለ እኔ ከታጋሾች ሆኜ ታገኘኛለህ አንተንም በምንም አልወነጅልህም" አለች፡፡
መሀመድም (ሰዐወ) "ከድጃ ሆይ አንቺ የተከበርሽና ባለብዙ ሀብት እኔ ደግሞ የአንቺ ተቀጣሪና ከምትሰጪኝ ገንዘብ ሌላ ምንም የለኝም እናም ገንዘብ የሌለው ፈልጎም ቢሆን ቢጤውን ያገባል" አላት፡፡


...ከድጃም እንዲህ አለችው "ገንዘቡን ብናደባልቀው ይበዛል እንጂ አያንስም"፡፡ ወጣቱም በድጋሚ ምንም ሳይመልስላት ዝም አለ፡፡
ከድጃም "በግልፅም ሆነ በድብቅ የሚሰሩትን የሚያውቅና የሚያይ በሆነው ጌታዬ ይሁንብኝ በኔ በኩል ምንም የሚሸፍነው ነገር የለም፡፡ ሁሉም ነገር እውነት ነው በል አሁን ወደ ቤተሰቦችህ ሂድና አጎትህን ለጋብቻ እንዲጠይቁኝ ንገራቸው፡፡ ምናልባት አባቴ ብዙ ገንዘብ ለኒካህ ከጠየቃቸው የጠየቀውን በሙሉ እኔ እሰጥሀለው፡፡ እኔ ያንተ ነኝ እኔው መረጥኩህ ከአንተ ሌላ ማንንም አልፈልግም፡፡ ልቀርብህ ሳስብ አትራቀኝ " አለችው ልመና በተቀላቀለበት አነጋገር፡፡
መሀመድ (ሰዐወ) ተነስቶ ከቤቷ ወጣ፡፡ ከድጃ መሀመድ (ሰዐወ) ከመምጣቱ በፊት ለወዳጅ ጓደኛዋ ለነፊሳ አጫውታት ነበር፡፡ ነፊሳም እሱን አሳምና ከምትወደው ሰው ጋር እንደምታጋባት ቃል ገብታላት ነበር፡፡ ወጣቱ መሀመድና ነፊሳ ሲገናኙ ነፊሳ ስለታላቋ ሴት ስለ ከድጃ መልካም ባህሪና እንዲሁም እሱን ማግባት እንደምትፈልግ ከገንዘቧ እንደምታስበልጠው አንድ በአንድ ነገረችው፡፡ ጥያቄዋን እንዲቀበልም አሳመነችው፡፡
ታላቁ ሰው አጎቱ ቤት ተመለሰ፡፡ አቡጣሊብን ከወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጋር ቤት ቁጭ ብሎ አገኛቸው፡፡ አጎትዬው በፈገግታ ተቀበሉት ከዚያም "ከድጃ ከከባድ ስጦታ ጋር እንደላከችህ እገምታለው" አሉት፡፡ መሀመድም "አጎቴ ሆይ ግምትህ ትክክል ነው፡፡ ከአንተ ጉዳይ አለኝ " አለ፡፡
አቡጣሊብም "ከአንተ ጉዳይ ጀርባ ጌታህ አለ፡፡ ለመሆኑ ምንድናት ጉዳይዋ" አሉት፡፡
መሀመድም "ሂዱና ከድጃን ለትዳር እንደምፈልጋት ቤተሰቧን ጠይቁና አምጡልኝ " አለ፡፡

የመሀመድ አጎቶች ተያዩ ከአቡጣሊብ በስተቀር ማንም ምንም መናገር አልፈለገም፡፡ አቡጣሊብም "ልጄ ሆይ ከድጃ እጅግ የተከበረችና በሰዎች ዘንድ የተወደደች ብዙ ሀብት ያላት ከአሁን በፊት ሁለት ሰዎች አግብታና በሞት የተለዩዋት ንብረታቸውን ወርሳ የምትኖር አሁን በቅርቡ ታላላቅ ሹማምንቶች ለጋብቻ ጠይቀዋት እንቢ ያለች ናት፡፡ አንተ የወንድሜ ልጅ ደግሞ ምንም ንግድ የለህም የርሷ ተቀጣሪ ነህ፡፡ ስለዚህ ራሷን አሳልፋ አትሰጥህም" አሉት፡፡
ሙሀመድም (ሰዐወ) "አጎቴ ሆይ አሁን ያልከውን በሙሉ አውቀዋለሁ እረዳሀለው የጋብቻ ጥያቄው ግን ከራሷ ነው የመጣው፡፡ " አላቸው
.
.
ይቀጥላል ኢንሻ አላህ

@tualibelilm
644 views14:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 23:05:51 እውነተኛ ፍቅር


ክፍል

የከድጃ ሀብት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጣ፡፡ በውክልና እሷ ዘንድ በኮሚሽን መቀጠር ከቻሉ ሰዎች መካከል ሙሀመድ (ሰዐወ) አንዱ ነበር፡፡ ወጣቱ ትሁት ሰው አክባሪ የሰውን ገንዘብ ያለ ሀቁ የማይፈልግ ታታሪ ቸር ስራውን ወዳድ በመሆኑ ከድጃ ጋር ከተቀጠረ ጀምሮ ከመካ ከተማ ርቆ በመሄድ እየነገደ ገንዘቧን በእጥፍ አሳደገው፡፡ በዚህም ከድጃ በወጣቱ ኮርታበታለች፡፡ ሙሀመድ ከድጃ ጋር የተቀጠረው እንዲሁ በአጋጣሚ አልነበረም፡፡ የሚያሳድጉት አጎቱ ጥሪት አነስተኛ በመሆኑ እንጂ፡፡
የሙሀመድ አባት አብደላህ ገና ሳይወለዱ ነበር የሞቱት፡፡ እናታቸውን ያጡት ደግሞ በ6 አመታቸው ነበር፡፡ ቢሆንም በአያቱ ዘንድ አደገ፡፡ አያቱ ሲሞቱ አጎቱ ተረከቧቸው፡፡
መሀመድ አጎቱ ጋር መኖር ሲጀምር ፍየል በመጠበቅ ተግባር ተሰማራ፡፡ ግን ብዙም ሳይቆይ አጎትየው የገቢያቸውን መጠን ለማሳደግ ጥረት ማድረግ ጀመሩ፡፡
አንድ ቀን ከድጃ ወንዶችን ወደ ምድረ ሻም በመላክ እንደምታሰማራ ስላወቁ ነጋዴው ወደተባለው ሀገር ለመጓዝ በዝግጅት ላይ ሳሉ ሙሀመድን አስጠርተው ስለሁኔታው ሊነግሯቸው ወሰኑ፡፡
"የወንድሜ ልጅ ሆይ እንደምታውቀው አንዳች የሌለኝ ደሀ ነኝ ፤ ግዜው ደግሞ በድርቅ ተመቷል፡፡ ከድጃ ሰው ቀጥራ እንደምታስነግድ ሰምቻለው በርግጥ የምትከፍለው ገንዘብ አነስተኛ በመሆኑ ደስ አያሰኝም፡፡ እናም ስለዚህ ጉዳይ እሷኑ ባነጋግርልህ " ሲሉ አቡጧሊብ ጥያቄ ለመሀመድ አቀረቡ፡፡ ሙሀመድም እንዲህ አላቸው "አጎቴ ሆይ እንዳሻህ ማድረግ ትችላለህ ሀሳብህ የኔም ሀሳብ ነው መጭው አለም ከዱንያ አለም በላጭ ነው" አሏቸው፡፡
አቡጧሊብ ጊዜ ማጥፋት አልፈለጉም ወንድሞቻቸውን አስከትለው ወደ ኸድጃ ቤት አመሩ፡፡ እሷም ከሀር በተሰራ ባማረ ልብስ ተውባ በፈገግታ ተቀበለቻቸው፡፡
አቡጧሊብም "የተከበርሽው ከድጃ ሆይ እኛ የመጣነው ለጉዳይ ነው ሰዎችን ገንዘብ እየከፈልሽ እንደምታስነግጂ ሰምቻለው፡፡ ለሌሎች በምትከፊይው ላይ ጨምረሽ ተመሳሳይ ስራ እንዲሰራልሽ መሀመድን አትቀጥሪምን? " አሉ
ከድጃም "እንኳንስ ለሚወደድ ለቅርብ ዘመድ ለማይታወቀውም ቢሆን ጥያቄዎ በኔ ዘንድ ተቀባይነት አለው" በማለት አስደሳች መልስ ሰጠች፡፡
አቡጧሊብ አስደሳቹን ዜና ይዘው ወደ መሀመድ (ሰዐወ) ተመለሱ፡፡ ብስራቱን ከነገሩት በኋላ "ይህ ፈጣሪ ላንተ የላከው ሲሳይ ነው " አሉ፡፡
ሩህሩሁ አጎት መጪው ጊዜ ያረገዘውን ቢረዱ ይህ ለከድጃ ከሰማይ የወረደ ፀጋ ነው ባሉ ነበር፡፡ ሆኖም ከዚህ መልካም ዜና በስተጀርባ የሚመጣውን የላቀ ዕጣ የሚያውቅ አንድም ሰው አልነበረም፡፡
እድለኛዋ ከድጃ አቡጧሊብ ያቀረቡትን ጥያቄ በደስታ ተቀበለች ፤ ይህም ሙሀመድ (ሰዐወ) እና ከድጃ (ረዐ) ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቁበት አጋጣሚ ፈጠረ፡፡ ጉዳዩ በመካ ነዋሪዎች ዘንድ ተዳረሰ፡፡ በየአጋጣሚው የታላቁን ሰው መልካም ትሩፋት እውነተኛነት ዘረዘሩላቸው፡፡ ከድጃም ይበልጥ ደስ አላት፡፡ መይሰራ ከተባለው አገልጋይ ጋር ወደ ሻም እንዲሄዱ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን አስታወቀች፡፡ ሙሀመድም የተሰጣቸውን አማና ተቀብለው ለንግድ ከመይሰራ ጋር ወደ ሻም አመሩ፡፡


የተከበረችው ከድጃ አንድ ምሽት ተኝታ ህልም አየች፡፡ ከእንቅልፏ እንደነቃችም ስላየችው ህልም ማሰብ ጀመረች በጃህሊያ ጊዜ ህልም ትልቅ ትርጉም ስለሚሰጠው ለህልም ፈቺዎች ለታላላቅ ሰዎች ይነገራቸውና ያስፈቱት ነበር፡፡ ከድጃም የህልሙን ፍቺ ለማወቅ ጓግታ አጎቷ ወረቃ ጋር ሄዳ ህልሟን ነገረችው፡፡

ህልሟም "ፀሀይ ከሰማይ ወየ ምድር ቀጥ ብላ በመውረድ ወደ ከድጃ ቤት በመግባት ቤቷ ውስጥ አበራ፡፡ ቤቱም በብርሀን ተሞላ፡፡ ቤቱም በብርሃን ተሞላ፡፡" ወረቃም ህልሙን በሰማ ጊዜ የጥሩ ጊዜ መምጫ መቃረቡን ተረዳ፡፡ ከዚያም ለከድጃ እንዲህ አላት
"የወንድሜ ልጅ የምስራች ቤትሽ የገባው የነቢይ ኑር ሳይሆን አይቀርም አላህ ሊያከብርሽና ሊያልቅሽ እንደሆነ እጠረጥራለሁ፡፡
ከድጃም "የነቢይ ኑር ምንድነው ?" አለችው፡፡ ወረቃም "የአላህ ብርሀን ነው ወደ ምድር የሚላክ ብርሀን የመጨረሻው ነቢይ መምጫው ተቃርቧል ሰዎችን ከጨለማ ወደ ብርሀን ይጠራል፡፡ ከፀሀይ መውጫ እስከ መግቢያ ያሉ ሰዎች ይከተሉታል፡፡ "
ከድጃ (ረዐ) ወረቃ በነገራት ነገር በጣም ተገረመች፡፡ በሌላ ጊዜ ከድጃ ከቁረይሽ ወይዛዝርት ጋር በካዕባ የክብር ቦታ ቁጭ ብላ ሳለ አንድ አይሁዳዊ "እናንተ የቁረይሽ ወይዛዝርቶች የነቢይ መምጫው ተቃርቧል፡፡ አደራችሁን ለሚመጣው ነቢይ ፍራሽ እንድትሆኑለት የመፅሀፉ ትንቢትም ደርሷል" አላቸው፡፡ ወይዛዝርቱ ግራ በመጋባት አዩት ተሳለቁበትም፡፡ ከድጃ ግን የወረቃ ንግግር ትዝ አላት፡፡
መሀመድ (ሰዐወ) እና መይሰራ ከሻም ተመለሱ፡፡ መይሰራም ስለጉዞው ስላጋጠመው ተአምራት በዝርዝር ለኸድጃ ነገራት፡፡ በጥሩ ትርፍም እንደተመለሱ አወጋት፡፡ ከድጃ ግን ከገንዘቡ ይልቅ የሙሀመድ ሁኔታ ባህሪው ከጉዞው ተአምራት ጋር ተዳምሮ በልቧ እንድትወደውና እንድታፈቅረው አደረጋት፡፡ ስለእሱ ማሰብ ጀመረች፡፡ እንዲህ አይነት ስሜት ከዚህ በፊት ተሰምቷት አያውቅም፡፡ በመደነቅም ለራሷ ጥያቄ ማቅረቧ አልቀረም፡፡ ለመሀመድ (ሰዐወ) የጋብቻ ጥያቄ ለማቅረብ ወሰነች፡፡ ለመሆኑ እርሷ የ40 አመት ወይዘሮ እንደመሆኗ ወጣቱ መሀመድ (ሰዐወ) የጋብቻ ጥያቄዋን ይቀበለው ይሆን? ጥያቄዋ መልስ ባያገኝስ ፤ የሙሀመድን ቤተሰቦች ፊት እንዴት ታያለች?
.
.
ይቀጥላል ኢንሻ አላህ

Share share


@tualibelilm
540 views20:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 08:14:34 እውነተኛ ፍቅር


ክፍል

በቅድመ ኢስላም በጃህሊያ ዘመን ወደ ኢስላም ጥሪ ከመጀመሩ በፊት አስራአምስት አመት ገደማ አንድ ውብና ተክለ ሰውነቱ ያማረ ወጣት ካዕባ አጠገብ ከሚገኘው በኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ (ረዐ) ቤት አጠገብ አለፈ፡፡
ወጣቱ ሲያዩት ፊቱ እንደ በድር ጨረቃ የፈካ ፤ መልከመልካም ፣ የዐይኖቹ ጥቁረት የበረታ ፣ የሽፋሽፍቶቹ ፀጉር ረዥም ፣ ፀጉሩ በጣም የጠቆረ ፣ አንገቱ መለሎ፣ አይኖቹ በተፈጥሮ የተኳሉ ፣ ቅንድቡ ቀጭን እና ረዥም ከሩቅ ሲያዩት እጅግ ሲበዛ ቆንጆ ሲቀርቡት ተወዳጅ ጥርሱ ነጭ አፍንጫው ቀጥ ያለ ነበር፡፡
በወቅቱ የከድጃ ቤትና የዳረል አሰድ ቢን አብድልዑዛ ፣ ቤት ከካዕባው ጥቂት እርምጃ ነበር የሚርቀው፡፡ አንድ የአይሁድ መነኩሴ በከድጃ ቤት ውስጥ ቁጭ ብሎ ሳለ መልከመልካሙን ወጣት አየው ፣ ከድጃንም ወጣቱ ተጠርቶ እንዲመጣ አዘዛት ፣ ወጣቱም በከድጃ አገልጋይ ተጠርቶ መጣ፡፡
አይሁዳዊው መነኩሴ ወጣቱን በትህትና ልብሱን ከትከሻው አካባቢ ገልጦ እንዲያሳየው ጠየቀው ፣ ወጣቱም እንደተጠየቀው አደረገ ፣ አይሁዳዊው ትከሻው አካባቢ ባየው አስደናቂ ነገር ተደሰተ አቅፎም ሳመው፡፡
ሁኔታውን ስትከታተል የነበረችው ከድጃ ለአይሁዱ "ይህንን ድርጊትህን ቁረይሾች ቢያዩህ አንተን ከመቅጣት ትዕግስት የላቸውም " አለች፡፡
በርግጥ የአይሁዱ ድርጊት ለምን እንደሆነ ከድጃን (ረዐ) የገባት ነገር የለም ፣ ወጣቱን ስታየው ፊቱ የፈካና የሚያምር አንደበተ ርቱዕ ነበር፡፡ በሌላ ጊዜ አይሁዱ ለከድጃ እንዲህ አላት፡፡
"በተውራትና በኢንጂል ኪታቦች ላይ ሰፍሮ እንዳየሁት የአንድ ብርቱ ሰው መምጫ እየተቃረበ ነው፡፡ ይህ ሰው የተወለደው እዚሁ በመካ ነው ፣ እናትና አባቱ በልጅነቱ ይሞታሉ ፣ አጎቱ ያሳድጉታል ወደ መዲናም ይሰደዳል ፣ የሻምን ስልጣን በእጁ ያደርጋል ፣ በመካ ያሉትን ጣኦታት በሙሉ ሰባብሮ በማስወገድ ካዕባን ንፁህ ያደርገዋል፡፡"
ከድጃ አይሁዱ የተረከላትን በጥሞና አዳመጠች ፣ በንግግሩም ተማረከች ልቧ ጓጓ ወጣቱንም ለማወቅ ፈለገች፡፡
በሌላ ጊዜ አጎቷ ወረቃን ስለዚው ጉዳይ ጠየቀችው ፤ ወረቃም ወደ ሻምና ሶሪያ በመሄድ የኢንጅልን መፅሀፍ ስላጠናና ስለመረመረ ይመጣል ተብሎ የተተነበየው ታላቅ ሰው ከቁረይሾች እንደሚያገባ በገንዘብ እንደምትረዳውና ከጎኑ እንደምትሆን አረጋገጠላት፡፡
.

የተከበረችው ኸድጃ በዝሆኖች አቆጣጠር ከ15 አመት ቀደም ብላ ከአባቷ ኩወይሊድ ኢብኑ አሰድ አብድልዑዛ ከእናቷ ፋጡማ ቢንቱ ዛኢዳ ተወለደች፡፡ ከድጃ ስሩ ከጠለቀ ጫፉ ከዘለቀ ከተከበረ ነገድና ቤተሰብ የተገኘች ናት፡፡ ከህፃንነቷ ጀምሮ የነገሮችን እውነታ የመከታተልና የማወቅ ጉጉቷ ከዕድሜዋ የላቀ ነበር፡፡ ስለ ንግድ አባቷ ከወንድሞቿ ጋር ሲወያዩ በአትኩሮት ትከታተል ነበር፡፡
ለአቅመ ሄዋን ስትደርስ ብዙ የጋብቻ ጥያቄ ይቀርብላት ጀመር፡፡ እሷ ግን በስሜት ተገፋፍታ ለምርጫ አልቸኮለችም፡፡ ጉዳዩን በጥልቀትና በስፋት በመመርመር ለምትወስደው አቋም ሚዛናዊ መለኪያዎችን መፈለግ ተቀዳሚ ተግባሯ ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን አቡሀላህ ኢብኑዚራራህን አገባች፡፡ ከሱም ህንድና ሀላህ የተባሉ ልጆችን አገኘች፡፡ ከድጃ ከአቡሀላህ ጋር ጥቂት አመታት እንደቆየች በሞት ተለያት፡፡ ከዚያ አቲቅ ኢብኑል ኩዘይምን አገባች፡፡ ከሱም አንድ ልጅ ከወለደች በኋላ አቲቅ በሞት ተለያት፡፡ ሀብትና ንብረቱን ወርሳ ተቀመጠች፡፡
ከባሏ ሞት በኋላ የተለያዩ ሰዎች ለጋብቻ ቢጠይቋትም ፍቃደኛ አልሆነችም፡፡ የወንድ አይነት እየተግተለተለ በተለያየ አቀራረብ ደጅ ቢጠናትም ስሜት አልሰጣትም፡፡
አላህ በረቀቀ ጥበብና ማንም በማይደረስበት ሚስጥሩ የማንነት መለኪያ የትልቅነት መገለጫ ሆነው ከቀረቡት ነገሮች ሁሉ እጅግ ብልጫ ያለውን መልካም ነገርን ሁሉ አጠቃሎ የያዘ ሰው አዘጋጅቶላት እንደነበር አስባውም አታውቅም፡፡
ከድጃ ጣኦት አላመለከችም፡፡በጃህሊያ ከጣኦት አምልኮ እንድትቆጠብ ያደረጋት ለአጎቷ ወረቃ ያላት ቀረቤታ ነው፡፡ ወረቃ ኢብኑ ኑፈይል የነሳራዎች መፅሀፍ ከቅድመ አያቶቹ ስለተሰጠው ይህንን መከተል መርጦ ስለነበር ብዙ ዕውቀቶችን ወደተለያዩ አገሮች ሄዶ ተምሮ ብዙ እውቀት ስላገኘ ከድጃ የባዕድ አምልኮ እንዳትከተልና እንድትጠላ አድርጓታል፡፡ የተረጋጋች በሳል ተፈጥሮዋ የሰከነ በመሆኑ ሰዎች "ጧሂራ"(ንፅህት) በሚል በልዩ የማዕረግ ስያሜ ይጠሯታል፡፡ ይህን ስያሜ ከእስልምና በፊት ያገኘችው ነው፡፡
አንድ ወቅት ከቁረይሽ ሴቶች ጋር ሆና በጃህሊያ ጊዜ አመታዊ በዓል በሚያከብሩበት የክብር ቦታ ቁጭ ብላ ሳለ አንድ ሰው ሴቶቹ አጠገብ ሲደርስ "እናንተ የመካ ሴቶች በናንተ ከተማ ነቢይ ሊመጣ ነው ስሙ አህመድ ይባላል፡፡ ከናንተ የቻለ ያግባው " ሲል ይጮሀል፡፡ ሴቶቹና ሌሎች ሰዎች ጭምር በድንጋይ እየደበደቡት አባረሩት፡፡ የተከበረችው ከድጃ ስትቀር
.
.
ይቀጥላል ኢንሻ አላህ
share በማድረግ ተባበሩን
522 views05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 20:15:31 የጀናዛ አስተጣጠብ
555 views17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 22:19:46
646 views19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 19:13:06
እንኳን ለኢድ አል ፈጥር በሰላም አደረሳቹ

عيدكم مبارك تقبل الله منا ومنكم صالحالأعمال
የተባረከ መልካም ኢድ ይሁንልን አላህ መልካም ስራችን ይቀበለን

ኢድ ሙባረክ

ኢዳችን የሰላምና የፍቅር ያድርግልን

ሂዳያ ቲቪ ቀጥተኛዉ መገድ
𝙝𝙞𝙙𝙖𝙮𝙖 𝙩𝙫 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙖𝙡
𝙝𝙞𝙙𝙖𝙮𝙖 𝙩𝙫 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙖𝙡
1.0K views16:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-29 09:15:50 ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።

"أهل السُّنة يتركون أقوال الناس لأجل السنة، وأهل البدع يتركون السُّنة لأجل أقوال الناس"

አህለሱናዎች የመልእክተኛውን ሱና በማስቀደም የሰዎችን ንግግር ይተዋሉ። የቢድአ ባለቤቶች ግን ለሰዎች ንግግር ብለው ሱናን ይተዋሉ።
الصواعق (4/1003)


https://t.me/kukusal
1.0K views06:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-24 21:34:30
አስቤዛው በዚህ መልኩ ተዘጋጅቶዋል
5ሊትር ዘይት
5ኪሎ ሩዝ
5ኪሎ ፍርኖ ዱቄት
10ኪሎ ቂንጬ
የፊታችን ቅዳሜ ይከፋፈላል የምትችሉት ለመለገስ @kimrim1 ላይ አናግሩን።

"ጾመኛን ያስፈጠረ የጾመኛው አጅር ሳይቀነስ የሱን ያክል ያገኛል። "




አል ፈላህ የበጎ አድራጎት ማህበር

https://t.me/Alfelahcharity
951 views18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-23 16:04:50 የ12ኛ ክፍል ዉጤት ይፋ ተደርጓል

ተማሪዎች የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ውጤታቸውን ማወቅ ይችላሉ።
1) በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት፡- result.neaea.gov.et
2) በትምህርት ሚኒስቴር ዌብሳይት፡- result.ethernet.edu.et
3) በቴሌግራም ቦት (Telegram Bot):- @moestudentbot - በዚህ ማስፈንጠሪያ በመግባትና Exam Result የሚለውን በመጫን በመልክት መጻፊያው ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት እና የ ምልክት በመጫን መላክና ውጤታቸው ማየት ይችላሉ።
4) በ9444 የ ኤስ ኤም ኤስ (9444 SMS) ፡- በመልክት ማስተላለፊያ መጻፊያ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ወደ 9444 በመላክ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
1.1K views13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-22 21:22:52
913 views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ