Get Mystery Box with random crypto!

ጥበቃ በር በሩን ይዜ ስራ ጀምሪያለው በገቡ በወጡት ፍተሻ ይዣለዉ አንዴ ቆም አንዴ ቁጭ ማለት | ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህንና ጥበብ

ጥበቃ

በር በሩን ይዜ ስራ ጀምሪያለው
በገቡ በወጡት ፍተሻ ይዣለዉ
አንዴ ቆም አንዴ ቁጭ ማለት ሳይታክተኝ
ድካም መሠላቸት ህመም ሳይሠማኝ
በብዙ ፈገግታ እጅግ እያበራው
አንተን በመጠበቅ ስራ ጀምሪያለው
መቼ ተስፋ ልቆርጥ መሽቶስ መች አርፌ
በአካል ባትመጣ ለፍልፌ በአፌ
ይመጣል አያድርም አይቀርም የምለው
እኩለ ቀን አልፎ እኩሌት ሚሆነው
እንዲያዉ አብሮኝ ባይቆይ ባይሆን ከጉያዬ
ምን ቸገረሽ ብሎ ባይሰማም ጉዳዬ
አይኖቼን ለማየት ይመጣል እያልኩኝ
ከበሩ ስር ሆኜ ጥበቃ ጀመርኩኝ
ሁሉም ስሜት ለካ ከሁለት ወገን ነው
አንድ በጥበቃ አንድ ትዝም አይለው
ቀናቶችን እርሳው እድሜህ ቢጋመስም
በፍለጋ ብዛት አፋሩን ብትምስም
መርፌ ከለገመ መች ሊወጋ ቂቤ
ትመጣለ ብዬ መጠበቅ ማሰቤ
አሁንስ ታከተኝ ጥበቃው ደከመኝ
ጉንበስ ቀና ማለት መጠበቅ ሰለቸኝ
29/02/2014
12:42 Pm

By Hiwi Dimple
@tsegaye_gebremedihen
@tsegaye_gebremedihen
@tsegaye_gebremedihen