Get Mystery Box with random crypto!

እባክሽ ወዴት ነሽ የት ይሆን መኖርያሽ ከሌሎች ተወስዶ እልፍ ልብ ያደለሽ ማን ቢመክርሽ ይሆን የ | ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህንና ጥበብ

እባክሽ ወዴት ነሽ የት ይሆን መኖርያሽ
ከሌሎች ተወስዶ እልፍ ልብ ያደለሽ

ማን ቢመክርሽ ይሆን የቱ ጥበበኛ
ዝቅ በዪ ያለሽ ለበረከት ማግኛ

ያ ሰው ነው ጥበባም አንቺን የወለደሽ
ልብ በሌለበት ልባም ያደረገሽ

እናትሽ ይሆኑ ወይስ የ አምላክ ጥበብ
ሚስጥር የነገሩሽ ዝቅታ አንደሚያስውብ

ጌቱ ቶሎሳ ነኝ / ይመለከተኛል
@tsegaye_gebremedihen
@tsegaye_gebremedihen
@tsegaye_gebremedihen