Get Mystery Box with random crypto!

ጥንቃቄ እና ማሳሰቢያ አዲሱ ከሳር ቤት በቄራ ጎተራ የሚሄደው ማሳለጫ መንገድ ላይ ከዚህ በፊት በ | Top Mereja

ጥንቃቄ እና ማሳሰቢያ

አዲሱ ከሳር ቤት በቄራ ጎተራ የሚሄደው ማሳለጫ መንገድ ላይ ከዚህ በፊት በወሬ ያየሁትን አሁን በዐይኔ ለማየት ችያለሁ።

በእርድ ወደ ቄራ የሚገቡ በሬዎች ሲበረረግጉ ወዳገኙበት አቅጣጫ መሮጣቸው ይታወቃል በዚህም ከዚህ በፊት አደጋዎች ሲያደርሱ እና ሲደርስባችሁ ተመልክተናል።

አሁን ባለው የቄራ ማሳለጫ መንገድ ላይ ግን ከዚህ በፊት ከሰማነው ለየት ያለ እና አደገኛ ሆኖ አይቻለሁ

ነገሩ እንዲህ ነው

ከበረት ለእርድ የሚገቡ ከብቶች ሲበረግጉ ወደ ማሳለጫው ሮጠው ከላይኛው አስፋልት ወደ ታችኛው (ወደ ዋሻው መግቢያ እና መውጫ) ይዘላሉ በዚህ ጊዜ ወደ ዋሻው እየገቡ እና እየወጡ ያሉ መኪኖች ላይ ይወድቃሉ በዚህም አንድ የቤት መኪና ላይ በሬ ወድቆ መኪና ውስጥ ያለ አንድ ወጣት መሞቱን የአካባቢው ሰዎች ነግረውኛል።

ይህንን አደጋ ከጊዜ በኃላ ድጋሚ በአይኔ አየሁ በሬ ተንደርድሮ ዘለለ እንደ አጋጣሚ መኪና ላይ አላረፈም ነገር ግን በአስፋልቱ ላይ ተፈጥፍጦ ተበታትኖ ሞተ! ነገሩ እጅግ ዘግናኝ ነው! እኔ ያየሁት በሬ ሰው ላይ ወይም ሚኪና ላይ ቢያርፍ ሰው እንደሚገድል እርግጠኛ ነኝ!

ይህንን የቄራ መሿለኪያ ዋሻ የምትጠቀሙ ሰዎች እባካችሁ በጣም ጥንቃቄ አድርጉ

የከብቶቹ ባለቤት ወይም የሚነዷቸው ሰዎች ይህ ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ እና የሚያስጠይቅ መሆኑን ይረዱ!

የሚመለከተው አካል በመንገዱ ላይ ከብትም ሆነ ሰው ማዘለል እንዳይችል የሚያግድ ነገር እንዲሰራበት ወይም ሌላ አማራጭ ተጠቅሞ ይህንን አሳሳቢ አደጋ እንዲከላከል እንጠይቃለን!

ወቅቱ የበዓል እንደመሆኑ በርከት ያሉ ከብቶች ለእርድ ወደ ቄራ ስለሚነዱ ከሌላው ጊዜ በላይ ጥብቅ ጥንቃቄ ያድርጉ መረጃውን ለሌሎች ሼር በማድረግ አድርሱ።

ማሳሰቢያውን ያደረሰን ሮቤራ አምሳሉ ነው!

@topMereja