Get Mystery Box with random crypto!

በጉራጌ ክልል ወልቂጤ በትራንስፖርት አገልግሎት አድማ መደረጉ ተሰማ  መንግስት አድማ ባደረ | የዛሬ መረጃ ®

በጉራጌ ክልል ወልቂጤ በትራንስፖርት አገልግሎት አድማ መደረጉ ተሰማ 

መንግስት አድማ ባደረጉ አሽከርካሪዎች ላይ  የነዳጅ ድጎማን እንደሚያነሳ አስጠንቅቋል


በጉራጌ ክልል ከወልቂጤ ወደ አዲስ አበባ ከአዲስአበባ ወደ ወልቂጤ የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል::የትራንስፖርት ማቆም አድማዉ የተደረገዉ ተሳፋሪዎች ከዚህ ቀደም ለአሽከርካሪዉ የሚከፍሉትን የመጓጓዣ ሂሳብ በተዘጋጁ መክፈያዎች ለመንገድ ትራንስፖርት እንዲከፍሉና መንገድ ትራንስፖርት ደግሞ ለመኪናዉ አሽከርካሪ በቴሌብር እንዲከፍል ሲደረግ ቀድሞ 250 የነበረዉ ክፍያ ወደ 170 ብር ዝቅ መደረጉም የቅሬታዉ ዋነኛ አካል ነዉ።

የክፍያ ስነስርዐቱ ወደ ዲጂታል መቀየሩ መልካም መሆኑን የተለያዩ የስፍራዉ አገልግሎት ሰጪዎች ቢናገሩም ነገር ግን ከወልቂጤ ወደ አዲስ አበባ ይሰራል ተብሎ የተቆፈረዉ መንገድ ሳይሰራ መኪናችን እየተጎዳ እንዲሁም በመንገዱ ላይ ባሉ ብዛት ያላቸዉ ትራፊኮች እየተጉላላን እና ይህንን ነገር ለመቅረፍ በመንግስት በኩል የትኛዉም እርምጃ ሳይወሰድ ታሪፍ መቀነሱ ለዚ አድማ መነሻ እንደሆነ ብስራት ሬድዮ ሰምቷል፡፡

በዚህም በዛሬዉ ዕለት ከወልቂጤ ወደ አዲስ አበባ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ወደ ወልቂጤ የትራንስፖርት አገልግሎት ባለመኖሩ ማህበረሰቡ እየተጉላላ ይገኛል፡፡ማህበረሰቡ እንዳይጉላላ በአስገዳጅ የተወሰኑ ተሽከርካሪዎች እንዲንቀሳቀሱ እየተደረገ መሆኑን እና አልሰራም ባሉ አሽከርካሪዎች ላይ ደግሞ የመንግስት የነዳጅ ድጎማን እንደሚነሳባቸዉ ማስጠንቀቅያ እየተሰጠ መሆኑን የወልቂጤ ከተማ የመንገድ ትራንስፖርት የስነምግባር ባለሙያ ይድየ ሙዲን ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

በአብርሃም ፍቅሬ
@TodayNewsEthiopia