Get Mystery Box with random crypto!

የ 'ጉማ አዋርድ' አዘጋጅ ዮናስ ብርሃነ ትናንት ምሽት በስካይ ላይት ሆቴል ከተካሄደው የሽልማት ስ | የዛሬ መረጃ ®

የ "ጉማ አዋርድ" አዘጋጅ ዮናስ ብርሃነ ትናንት ምሽት በስካይ ላይት ሆቴል ከተካሄደው የሽልማት ስነ ስርአት በኋላ ለእስር ተዳርጓል

በስፍራው ከነበሩ ሰዎች በደረሰኝ መረጃ መሰረት ዮናስን ሲቪል የለበሱ ደህንነቶች ከምሽቱ 5 ሰአት ገደማ ከነባለቤቱ አስረው ወስደዋቸዋል። ባለቤቱ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ብትፈታም ዮናስ አንበሳ ጋራዥ አካባቢ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኝ ታውቋል።

በትናንትናው ፕሮግራም ላይ "ልጅ ማኛ" በሚል የምትታወቀው ቲክቶከር ባደረገችው ሜካፕ ምክንያት "ልጅቷን አምጡ" በሚል አዘጋጆቹ ተጠይቀው እንደነበር እና እስሩም ከእሱ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል በስፍራው የነበሩ ግለሰቦች እና ሌሎች ምንጮች አረጋግጠውልኛል።

Elias Meseret