Get Mystery Box with random crypto!

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ የ2014 ዓ.ም | Ministry of education®

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ

የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ብሄራዊ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ለመስጠት የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እና የማዕከላዊ ጎንደር ትምህርት መምሪያ ሃላፊዎች በጋራ መስከረም 18/2014 ዓ.ም በማራኪ ግቢ መሰብሰቢያ አዳራሽ በፈተናው ዙሪያ እስከአሁን የተሰሩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ግምገማ አካሄዱ።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲም በጎንደርና በአካባቢው የሚገኙ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስፈተን እያደረገ ያለውን ቅድመ ዝግጅት በተመለከተ በዋናነት የሚያስፈልጉ ግብአቶችን በማሟላት ፈተናውን ስኬታማ በሆነ መንገድ ለማጠናቀቅ የተለያዩ ኮሚቴዎችን አቋቁሞ ወደ 43 ሺ ተማሪዎችን ለመቀበል የመፈተኛ ክፍሎች፣ የተማሪ አቀባበል፣ የመኝታ፣ የመብራትና የውሃ አገልግሎት፣ እንዲሁም የምግብ ግብአትና ልዩ ልዩ ግብአቶችን አስቀድሞ የማሟላት ስራ እየተሰራ መሆኑን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን ገልፀዋል።

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER