Get Mystery Box with random crypto!

በአማራ ክልል በቅርቡ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች የተላለፈ አስቸኳይ መ | Ministry of education®

በአማራ ክልል በቅርቡ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች የተላለፈ አስቸኳይ መልዕክት፡፡

የ2014 /2015 ዓ.ም በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በክልሉ ባሉ ዩኒቨርስቲዎች ፈተናው እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወሳል፡፡

በመሆኑም ተፈታኝ ተማሪዎች ቀድመው ሊዘጋጁባቸው የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች እንደሚከተለው ይቀርባሉ፡፡

1. ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ማዕከልም ይሁን በመፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ መገኘት ግዴታ በመሆኑ አድሚሽን ካርድ ፎርም ከሞሉበት ትምህርት ቤት እና ወረዳ በአካል በመገኘት እስከ መስከረም 10/2015 ዓ.ም እንዲረከቡ፡፡

2. በአድሚሽን ካርዱ ላይ የስም፣ የስትሪም እና የጾታ ወዘተ..ስህተት ካለ በአስቸኳይ ለትምህርት ቤቱ እና ለወረዳው ሪፖርት እንድታደርጉ በጥብቅ እያሳሰብን ይህንን የማያደርጉ ተማሪዎች ካሉ ፈተና ለመውሰድ እንደሚቸገሩ፤

3. ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጡ የትምህርት ቤት ወይም የኗሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት የሚገባ መሆኑ፤

4. ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ጊዜ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ ይዘው መገኘት ያለባቸው መሆኑ ከዚህ ዉጭ ሌሎች ቁሳቁሶችን በዩኒቨርሲቲ ግቢ እና በመፈተኛ ክፍል መያዝ የተከለከለ መሆኑ፤

5. ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች ትምህርት ቤቱ፣ ወረዳው እና ዞኑ በሚያዘጋጀው የጉዞ ፕሮግራም መሰረት ወደ መፈተኛ ዩኒቨርሲቲ የሚጓዙ መሆኑን በመረዳት ዝግጅት ማድረግ ያለባቸው መሆኑን፤

6. ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ተመደበበት ዩኒቨርሲቲ ሲሄድ አንሶላ፣ ብርድልብስና የትራስ ልብስ ይዞ የመምጣት ይኖርባቸዋል፡፡

ይህን መረጃ ሸር በማድረግ ለተማሪዎችና ተማሪ ወላጆች እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት እንዲደርስ ትብብራችሁን እንድታደርጉ በተፈታኝ ተማሪዎች ስም ቢሮው ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
ባህርዳር

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ ! !

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER