Get Mystery Box with random crypto!

በ2015 በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል) አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ሙሉ ለሙ | Ministry of education®

በ2015 በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል) አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንደሚሆን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በተመሳሳይ፣ የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት ከኹሉም ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች በተመረጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሙከራ ትግበራ ይጀመራል ሲሉ የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ሥራ አስፈጻሚ አመለወርቅ ህዝቅኤል ተናግረዋል።

በአገር አቀፍ ደረጃ ሰኞ መስከረም 9 ቀን 2015 ለሚጀመረው ትምህርት የተለያዩ ዝግጅቶች ማድረጉን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።ሰኞ ዕለት በይፋ ለሚጀመረው ትምህርት በአብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች የመክፈቻ ሥነ ስርዓት እንደሚያካሄድም አመለወርቅ ገልጸዋል።

ተማሪዎች ደስ ብሏቸው የትምህርት ቀኑን እንዲጀምሩ የተለያዩ ዝግጅቶች በየትምህርት ቤቶቹ እንደሚካሄዱ የገለጹት ኃላፊዋ፣ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ በክልል ያሉ ትምህርት ቢሮዎች፣ ትምህርት ቤቶች እና የተለያዩ ድርጅቶች በትምህርት ቤት ውስጥ መዝናኛ ዝግጅት አዘጋጅተው ተማሪዎችን የመቀበል ሥነ ስርዓት ያካሄዳሉ ብለዋል።

የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች፣ መምህራንን እና ማህበረሰቡ በትምህርቱ የጊዜ ሰሌዳ እና በሥርዓተ ትምህርቱ አፈጻጸም ላይ ውይይቶችን እንዳደረጉ ወ/ሮ አመለወርቅ መጠቆማቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሥራ ከመጀመራቸው በፊት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየቱን ያወሱት የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊዋ፣ በዚህም የትምህርት ቤቶች እድሳት፣ የአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የመጽሐፍት ማስተዋወቅ እና የትምህርት ጉባዔ የማካሄድ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል።

https://t.me/Tmihirt_Minister
https://t.me/Tmihirt_Minister