Get Mystery Box with random crypto!

71 ሺ 832 ተማሪዎች የሚፈተኑበት የዘንድሮው የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ሰኔ 27 ይጀምራል። | Ministry of education®

71 ሺ 832 ተማሪዎች የሚፈተኑበት የዘንድሮው የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ሰኔ 27 ይጀምራል።

የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 29 እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ዳኘው ገብሩ በፈተናው አሰጣጥ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫው የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በከተማዋ በ 792 ትምህርት ቤቶች እንደሚሰጥ ተነግሯል።

ለዚህም 179 የመፈተኛ ጣቢያዎች ተዘጋጅተዋል ብለዋል ።

አቶ ዳኘው አክለውም አጠቃላይ በከተማዋ 71 ሺህ 832 ተማሪዎች እንደሚፈተኑ ነው የተናገሩት።

ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ እስካሁን ያለውን የፈተናው ዝግጅት ሂደት የገመገመ ሲሆን ፈተናው ወደ መፈተኛ ጣቢያዎች ለማጓጓዝ ሂደት ላይ ነውም ተብሏል።

ሰኔ 24 ቀንም ለሁሉም ፈተናውን ለሚመለከት የትምህርት ማህበረሰብ ኦረንቴሽን እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡

(አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ)

ለጓደኛዎ ሼር ያድርጉ

@TMIHIRT_MINISTER
@TMIHIRT_MINISTER