Get Mystery Box with random crypto!

የጀነት ዛፍ በቁርአን እና በባይብል “ጀናህ” جَنَّة የሚለው ቃል “ጀነ” جَنَّ ማለትም “ | Tiriyachen | ጥሪያችን

የጀነት ዛፍ በቁርአን እና በባይብል

“ጀናህ” جَنَّة የሚለው ቃል “ጀነ” جَنَّ ማለትም “ተሰወረ” ወይም “ተደበቀ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ድብቅ” ወይም “ስውር” ማለት ነው፥ በጀነት ውስጥ ያለው ለሙሥሊሞች የተደበቀላቸውን ፀጋ ደግሞ ማንኛይቱም ነፍስ ስለማያውቅ ድብቅ እና ስውር ነው። በሐዲሰል ቁድሢይ ላይ የተዘጋጀው የጀነት ጸጋ ዓይን ዓይቶት፣ ጆሮ ሰምቶት፣ ልብ አስቦት የማያውቅ መሆኑ ተገልጿል፦

ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን ጸጋ ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም፡፡
ሱራ አስ ሳጂድ 32፥17

አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ ነብዩ እንዲህ ብለው አሉ፦ “አላህም እንዲህ አለ፦ እኔ ለደጋግ ባሮቼ ዓይን ዓይቶት የማያውቅ፣ ጆሮ ሰምቶት የማያውቅ እና በሰው ልቦና ውል ብሎ የማያውቅ ጸጋን አዘጋጅቻለው”።
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 123

ስለዚህ በጀነት ውስጥ ያሉትን አሏህ ለባሮቹ ያዘጋጃቸው ፀጋዎች ዓይን ዓይቶት፣ ጆሮ ሰምቶት፣ ልብ አስቦት የማያውቅ ከሆነ ጀነት ውስጥ ያለው ሙዝ፣ ዘንባባ፣ ወይን፣ ተምር እንዲሁ ዛፍ ከዱንያው ውስጥ ካለው ነገር ጋር የስም መመሳሰል እንጂ ቅርጽና ይዘቱ አሊያም ጥፍጥናውና ጣዕሙ አንድ አይደለም፦

ዛፎችዋም በእነርሱ ላይ የቀረበች እና ፍሬዎችዋም ለለቃሚዎች መግገራትን የተገራች ስትኾን ገነትን መነዳቸው፡፡
ሱራ አል ኢንሳን 76፥14

አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም እንዲህ አሉ፦ “በጀናህ ውስጥ በጥላ ሥር ፈረሰኛ መቶ ዓመት የሚምታስጓዝ ዛፍ አለች”።
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 53 ሐዲስ 7

ጊዜ የሚለካው በሰከንድ፣ በደቂቃ፣ በሰዓት፣ በቀን፣ በወር፣ በዓመት ሲሆን በተመሳሳይ ከሜትር ቁጥጥር ውጪ ያለ ርዝመት የሚለካው በዓመት ነው፥ በፈረሰኛ መቶ ዓመት መገለጹ በራሱ ጀናህ ምን ያክል ሰፊ እንደሆነች በቀላሉ መረዳት ይቻላል። ቀለብ እንጂ ቀልብ የሌላቸው ሚሽነሪዎች በጀናህ ውስጥ ዛፍ መኖሩ ለመሳቅ እና ለመሳለቅ ሲቃታቸው ዓይተን ነበር፥ እንዚህ ዘንጋታዎች እየተጎማለሉ እና ዘንፈል እያሉ ቁርኣን እና ሐዲስ ውስጥ እንደገቡ እኛም እንዲማሩበት በጨዋ ደንብ እና ሥርዓት ከባይብል በጀነት ውስጥ ዛፍ እንዳለ ጠቅሰንና አጣቅሰን እናቀርባለን፦

በእግዚአብሔርም ገነት በዔድን የነበሩ “ዛፎች” ሁሉ ቀኑበት።
ሕዝቅኤል 31፥ 9

ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት “ዛፍ” እንዲበላ እሰጠዋለሁ።
ራእይ 2፥7

በወንዙም ወዲያና ወዲህ በየወሩ እያፈራ አሥራ ሁለት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት “ዛፍ” ነበረ፥ የዛፉም ቅጠሎች ለሕዝብ መፈወሻ ነበሩ።
ራእይ 22፥2

እነዚህ ሦስት አናቅጽ ላይ በገነት ውስጥ ዛፎች እንዳሉ አስረግጠውና ረግጠው ያስረዳሉ፥ “የሕይወት ዛፍ” ማለት አዳም እና ሔዋን በገነት እያሉ እንዲበሉት የበቀለ ዛፍ ነው፦

በገነትም መካከል “የሕይወትን ዛፍ”፥ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ።
ዘፍጥረት 2፥9

እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤
ዘፍጥረት 2፥16

እሥልምና እንዲጠፋ ሙሥሊም እንዲገፋ ቀን ከሌሊት የሚዋትሩ እነዚህ እብሪተኞች እና ዳተኞች የሚሰበሰቡበት አዳራሽ ክበብ ይሁን ክለብ ለይተው ሳያውቁ እነዚህ አናቅጽ ያነቡአቸዋል ብለን አናስብም፥ ሚሽነሪዎች ሆይ! መቅኖ አጥታችሁ መቀመቅ ከመውረዳችሁ በፊት ጨርቄን እና ማቄን ሳትሉ ወደ ዱኑል ኢሥላም እንድትመጡ ጥሪአችን ነው። አምላካችን አሏህ ለኢሥላም ጸር እና አጽራር ከመሆን አርነት አውጥቶ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። 

ለተጨማሪ ንባብ ድረገጻችንን ይጎብኙ።
https://tiriyachen.org/?p=4066
‐‐‐
Follow us on:
‐‐‐
https://fb.me/tiriyachen 
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen