Get Mystery Box with random crypto!

ቡሄ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን | Tiriyachen | ጥሪያችን

ቡሄ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና። وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

መጣና መጣና
ደጅ ልንጥና፤
መጣና ባመቱ
እንዴት ሰነበቱ፣
ክፈት በለዉ በሩን
የጌታዬን፣
ክፈት በለዉ ተነሳ
ያንን አንበሳ፣
መጣሁኝ በዝና
ተዉ ስጠኝ ምዘዝና።
እየተባለ ሆያ ሆዬ በልጅነት ያለ ዕውቀት ሙሥሊሙ ከክርስቲያኑ ጋር ተደባልቆ የክርስቲያን ሠው ሥራሽ በዓል ሲያከብር አድጓል። "ቡሄ" ማለት "ገላጣ" "የተገለጠ" ማለት ነው፥ በአገራችን የክረምቱ አፈና ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታየውም በዚህ በዓል አካባቢ ስለሆነ ይህ ዕለት "ቡሄ" ተባለ። ኢየሱስ ሦስቱን ተከታዮች ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ አወጣቸው፦
ማቴዎስ 17፥1 *ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው*።

ይህ ተራራ የትኛው ተራራ እንደሆነ በባይብል አልተጠቀሰም። አንዳንድ ምሁራን አርሞንኤም ነው ይላሉ፥ የእኛዎቹ ታቦር ነው ይላሉ። "ደብር" ማለት የግዕዝ ቃል ሲሆን "ተራራ" ማለት ነው፥ የደብር ብዙ ቁጥር "አድባር" ሲሆን "ተራሮች" ማለት ነው። "ደብረ-ታቦር" ማለት "የታቦር ተራራ" ማለት ነው፥ ይህ ቡሄ በዓል ደብረ-ታቦር ይባላል።
በባይብል የተራራው ስም የለም፣ ይህ እለት ነሃሴ 13 ነው የሚል የለም፣ ይህንን ቀን አክብሩ የሚል የለም፣ በዚህ ቀን ዳንኪራ ሆያ ሆዬ አድርጉ የሚል የለም። ይህ ሁሉ ሰው ሠራሽ ሕግ ነው። በገጠርም ሆነ በየከተማው ልጆች ጅራፋቸውን ገምደው ሲያጮሁ ይሰነብታሉ። እናቶችም ለበዓሉ ዝግጅት ስንዴ ሲለቅሙ፣ ሲፈትጉ፣ ሲፈጩ ይሰነብታሉ። ቡሄ ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ በመስጠት እና ችቦ በማብራት በዓሉን ያከብራሉ። ይህ ሁሉ ከንቱ እዚሁ የሚቀር ምድራዊ ነገር ነው። ይህንን የክርስትና ሰው ሰራሽ በዓል ሙሥሊሙ ባለማወቅ ሲያከብረው ኖሯል። ይህ ስህተት ነው። ነቢያችን”ﷺ” የነገሩን ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻና ብቻ ናቸው፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ : መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን። አሏቸው። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፥ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” በሁለቱ በአል በኢደል አደሐ እና ኢደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ صِيَامَيْنِ يَوْمِ الأَضْحَى وَيَوْمِ الْفِطْرِ ‏.

ቡሄ የአገር ባህል ይመስለን ነበር፥ ቅሉ ግን እንደዛ አይደለም። ይህንን በዓል መልእክተኛው ያልሰጡን ዕቡይ ተግዳሮት መሆኑን ዐውቀን መሳተፍ የለብንም። የታሪክ ምፀት ከዐሊሞቻችን ለሚቀጥለው ትውልድ የሚሆን ሰፊ ምዕላድ ትተን መሄድ ግድ ይለናል፥ ይህን ለማድረግ አስረግጦ እና ረግጦ መረዳትና ማስረዳት ይጠበቅብናል። ያኔ የኢሥላም ልዕልና ለካፊሩን የልብ ፍልጠት፣ የራስ ምታት፣ የሆድ ቁርጠት፣ የጎን ውጋት እና የእግር ቁርጥማት ኢንሻላህ ይሆናል።

ለተጨማሪ ንባብ ድረገጻችንን ይጎብኙ።
https://tiriyachen.org/?p=4050
‐‐‐
Follow us on:
‐‐‐
https://fb.me/tiriyachen 
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen