Get Mystery Box with random crypto!

ሚሽነሪዎች፦ “የሒጃብ አንቀጽ መውረድ ምክንያት ዑመር ነው” ይላሉ። ታዲያ ምን ችግር አለው? ሳራ | Tiriyachen | ጥሪያችን

ሚሽነሪዎች፦ “የሒጃብ አንቀጽ መውረድ ምክንያት ዑመር ነው” ይላሉ። ታዲያ ምን ችግር አለው? ሳራ ለአብርሃም፦ “ይህችን ባሪያ ከነልጅዋ አሳድድ! የዚህች ባሪያ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አይወርስም” ብላ አሳቡን አምጥታ እግዚአብሔር ለአብርሃም አሳቧን እንዲቀበል፦ “ሣራም የምትነግርህን ቃል ሁሉ ስማ” ሲለው ለአጋር ብላቴናውንም ሰጥቶ አስወጣት፦

አብርሃምንም “ይህችን ባሪያ ከነልጅዋ አሳድድ! የዚህች ባሪያ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አይወርስምና” አለችው።
ዘፍጥረት 21፥10

እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፦ “ስለ ባሪያህና ስለ ብላቴናው አትዘን፤ ሣራም የምትነግርህን ቃል ሁሉ ስማ”።
ዘፍጥረት 21፥12

አብርሃምም ማልዶ ተነሣ፥ እንጀራንም ወሰደ፥ የውኃ አቁማዳንም ለአጋር በትከሻዋ አሸከማት፥ ብላቴናውንም ሰጥቶ አስወጣት።
ዘፍጥረት 21፥14

እግዚአብሔር አብርሃምን ያዘዘው ሳራ ባመጣቸው አሳብ ነው። የሒጃብ እሳቤ ዑመር ከመምጣቱ በፊት እኮ ባይብል ላይም አለ። ይስሐቅም ርብቃን ከማግባቱ በፊት አጅነቢይ ስለነበረ እንዳያያት ኺማር ወስዳ ተከናነበች።

እርስዋም መሸፈኛ ወስዳ ተከናነበች።
ዘፍጥረት 24፥65

ለተጨማሪ ንባብ ድረገጻችንን ይጎብኙ።
https://tiriyachen.org/?p=3911


መልካም ቆይታ ከጥሪያችን ጋር
‐‐‐
Follow us on:
‐‐‐
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen