Get Mystery Box with random crypto!

እኛ ሙሥሊሞች፦ “ዐበይት ክርስትና ማለትም ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ እና አንግሊካን ማርያምም ያመልካሉ” | Tiriyachen | ጥሪያችን

እኛ ሙሥሊሞች፦ “ዐበይት ክርስትና ማለትም ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ እና አንግሊካን ማርያምም ያመልካሉ” ስንል በተቃራኒው እነርሱ፦ “እናከብራታለን እንጂ አናመልካትም” ብለው ዓይናቸውን በጨው አጥበው ይዋሻሉ፥ ምክንያቱም “እናመልካታለን” ካሉ አምልኮ የሚገባው አንድ አምላክ እንደሆነ ባይብል ላይ በቅጡ ሰፍሯል፦

"ልባችሁንም ወደ ያህዌህ አቅኑ፥ እርሱንም ብቻ አምልኩ።"
1ኛ ሳሙኤል 7፥3

"ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ።"
ማቴዎስ 4፥10

ይህንን ጥቅስ ሲያዩ ጭራሽ ወደ ማርያም፦ “ከልጅሽ ጋር አስታርቂን ብለን እጠይቃታለን እንጂ ወደ እርሷ አንጸልይም” የሚል ቅጥፈት ይቀጥፋሉ።

፨ ሲጀመር ሁሉን ዐዋቂ፣ ሁሉን ሰሚ እና ሁሉን ተመልካች አንዱ አምላክ ሆኖ ሳለ የማወቅ፣ የመስማት እና የመመልከት ውስንነት ያለበትን ፍጡር በሌለበት መለማመን ሆነ መጠየቅ ሺርክ ነው።

፨ ሲቀጥል ወደ ማርያም ድብን አርጋችሁ ትጸልያላችሁ፥ የአዋልድ መጻሕፍቶቻችሁ ይህንን ያሳብቃሉ፦

“እኔ በዚህ ጸሎት በጸለይሁ ጊዜ ወደ አንደበቴ ነገር ጆሮሽን ዘንበል አድርገሽ ስሚ፥ ሰምተሽም ቸል አትበይ። በብሩኅ ልቦና በንጹሕ አሳብ የአንደበቴን ነገር ተቀበይው እንጂ።”
መጽሐፈ አርጋኖን ዘሰኞ ምዕራፍ 2 ቁጥር 1

“እርሷን “ደስ ይበልሽ” እያልን ይቅርታ እንድትሰጠው ወደ እርሷ እንጸልያለን።”
ክብረ ድንግል ማርያም 1

ለተጨማሪ ንባብ ድረገጻችንን ይጎብኙ።
https://tiriyachen.org/?p=3898

መልካም ቆይታ ከጥሪያችን ጋር
‐‐‐
Follow us on:
‐‐‐
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen