Get Mystery Box with random crypto!

“እነዚያ ያመኑ፣ መልካም ሥራዎችንም የሠሩ፣ ሶላትንም ያስተካከሉ፣ ”ዘካንም የሰጡ ለእነርሱ በጌታቸ | Tiriyachen | ጥሪያችን

“እነዚያ ያመኑ፣ መልካም ሥራዎችንም የሠሩ፣ ሶላትንም ያስተካከሉ፣ ”ዘካንም የሰጡ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፡፡ በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም እነርሱም አያዝኑም”፡፡
ሱራ አል ኢምራን 2፥277

“ዘካህ” زَكَاة የሚለው ቃል “ዘካ” زَكَىٰ ማለትም “ጠራ” ከሚል የግስ መደብ የመጣ ሲሆን “መጥራራት” ማለት ነው፦

“ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የመኖሪያ ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ አሏቸው፡፡ ይህም “የተጥራራ” ሰው ምንዳ ነው፡፡
ሱራ ጣሀ 20፥76

“የተጥራራ” ለሚለው ግስ የገባው ቃል “ተዘካ” تَزَكَّىٰ ሲሆን የስም መደቡ “ዘካህ” زَكَوٰة ነው። ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን ሸሪዓዊ ፍቺው ደግሞ “የግዴታ ምጽዋት” ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ ከሰጠን ሲሳይ ላይ የምንለግሰው ልግስና ዘካህ ይባላል፦

“እነዚያ ያመኑ፣ መልካም ሥራዎችንም የሠሩ፣ ሶላትንም ያስተካከሉ፣ ”ዘካንም የሰጡ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፡፡ በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም እነርሱም አያዝኑም”፡፡
ሱራ አል ኢምራን 2፥277

“እነዚያ ሶላትን ደንቡን አሟልተው የሚሰግዱ ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚለግሱ ናቸው”፡፡
ሱራ አል አንፋል 8፥3

ዘካን የሚሰጡ አላህ ዘንድ ምንዳ አላቸው፥ በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም እነርሱም አያዝኑም።

ሙሉ ጽሁፉን ጥሪያችን ድረገጽ ላይ ያገኙታል።
https://tiriyachen.org/?p=3815
----------------------------
Tiriyachen|ጥሪያችን
#ዘካህ
#ምፅዋት
#TiriyachenArticles

Follow us on:
----------------------------
https://fb.me/tiriyachen
https://t.me/tiriyachen
https://tiriyachen.org