Get Mystery Box with random crypto!

የፕሮቴስታንቱ ቸርች የማይፈታው እንቆቅልሽ! #መፅሐፍ #ቅዱስን ልዩ ከሚያረጉት ነገሮች | ትንሳዔ ዘኢትዮጵያ ✝✝✝

የፕሮቴስታንቱ ቸርች የማይፈታው እንቆቅልሽ!

#መፅሐፍ #ቅዱስን ልዩ ከሚያረጉት ነገሮች መካከል አንዱ ዕድሜው ነው ከሱ ቀድሞ ወይም ከሱ በፊት የተፃፈ መፅሐፍ የለም የመጀመሪያው መፅሐፍ መፅሐፈ ሄኖክ ሲሆን የተፃፈውም ከአዳም ጀምሮ #ሰባተኛ #ትውልድ በሆነው በሄኖክ በ 1486 ዓመተ ዓለም ወይም ከክርስቶስ ልደት 4014 ዓመት በፊት ነው " #የአምላካችን #ቃል #ግን #ለዘላለም #ፀንታ #ትኖራለች " ት.ኢሳ 40 ፥ 8 እንደተባለ
መፅሐፍ ቅዱስ ታሪክ የማይሽረው ዘመን የማይገታው የማያረጅ #ዘላለማዊ #ነው።

መፅሐፍ ቅዱስን #ከአርባ #ስምንት በላይ የሆኑ ጻሕፍት

እረኛ የነበሩ {ሙሴ ፣ አሞፅ }
ነገሥታት የነበሩ {ዳዊት ፣ ሰለሞን}
ካህን የነበሩ { ሕዝቅኤል }
ቀራጭ የነበሩ {ማቴዎስ }
ዓሳ አጥማጅ የነበሩ {ጴጥሮስ ፣ ዮሐንስ }
ሐኪም የነበሩ { ሉቃስ }
ከተለያየ የሥራ መስክ ተጠርተው ፤
በተለያየ ቦታ ማለትም ፦
በሲና ምድረ በዳ ፣
በኢየሩሳሌም ፣
በተለያዮ የእስራኤል ክፍሎች
በስደት አገር በባቢሎን ፣ በፋርስ ፣በሮም ከተማ ፣ በፍጥሞ ደሴት በወህኒ ቤት ሆነው በተለያዩ ዘመናት የጻፉት የቅዱሳት መጻሕፍት ስብስብ ቢሆንም መልዕክቱ ግን ያልተዛባ ርቱዕ {ቀጥተኛ} የሆነ #እርስ #በርሱ #የማይጋጭ #ነው #ምክንያቱም #በእግዚአብሔር #መንፈስ #እየተመሩ #ፅፈውታልና ። ለብዙዎች እንደሚመስላቸው ቅዱሳት መጻህፍት #በአንድ #ጊዜ #ተፅፈውና #ተጠርዘው #የተገኙ #ሳይሆኑ #ለየብቻቸው #በብራና እየተጻፉ #ተጠቅልለው #ይቀመጡ #ነበር "የነቢዮንም #የኢሳያስን #መፅሐፍ ሰጡት #መጽሐፋንም #በተረተረ #ጊዜ ..." ሉቃ 4 ፥ 17- 20 #እንደተባለ እንዲሁም #ቅዱስ #ጳውሎስ ጢሞቲዎስን " ስትመጣ በጢሮአዳ ከአክርጳ ዘንድ የተውሁትን በርኖሱንና #መጻሕፍቱን ይልቁንም #በብራና የተጻፋትን አምጣልኝ " እንዳለው 2ኛ. ጢሞ 4 ፥ 13 አብዛኛው የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት በዕብራይስጥ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ደሞ በግሪክ ቋንቋ ተፅፈዋል ፤ በአዲስ ኪዳን ዘመንም እስከ 5ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መፅሐፍ ቅዱስ የተተረጎመባቸው ለመፅሐፍ ቅዱስ ነጠላ ትርጓሜ መሠረታውያን ( እንደ ሪፈራንስ ) የሚያገለግሉ ቋንቋዎች የሚባሉት ፦

#ግዕዝ (ኢትዬጵያ ) #ቮልጌት {ሮማይስጥ #የጥንቱ #ላቲን } #ኮብት {ግብፅ ቅብጥ} #ሱርስት { ሶሪያ }
#አርመንኛ { አርመን } #ናቸው በነዚህ #ቋንቋዎች #የተተረጎሙት መፅሐፍ ቅዱሳት በአሁኑ ጊዜ በጣም አስፈላጊ
ሆነዋል ምክንያቱም መፅሐፍ ቅዱስ የተጻፈባቸው መሠረታውያን ቋንቋዎች በመሆናቸው በየጊዜው ለሚነሱ ስህተቶች ማረሚያ ስለ ሆኑ ነው። ቅዱሳት መጻሕፍትን መሰብሰብ የተጀመረው የመጀመሪያው መፅሐፍ ከተጻፈበት ጊዜ ጀምሮ ሲሆን ብዛታቸውንና ዓይነታቸውን ለይቶ ለማወቅ ከፍተኛ ጥረት የተደረገው በአዲስ ኪዳን በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን በሐዋርያት ነው ፤ ሐዋርያት አጠቃላይ ስለ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን 85 ቀኖናትን ደንግገዋል ከነዚህም ውስጥ 85ኛው ድንጋጌ (ቀኖና) #ስለ #ቅዱሳት #መጻሕፍት #የሚናገር #ነው፤ ከዚያም በ325 ዓም በኒቂያ በተካሄደ ጉባኤ ላይ እውነተኞቹን ቅዱሳት መጻሕፍት ለመሰብሰብ በተወሰነው መሠረት ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ በ367 ዓም እውነተኞቹን የቅዱሳት መጻሕፍትን ቁጥርና ዓይነት አስታውቋል እንዲሁም ፤ በ393 ፣ በ399 ፣ እና በ419 ዓም እ.ኤ.አ በሰሜን አፍሪካ (ካርቴጅ ) በተካሄደ ጉባኤ ቅዱሳት መጻሕፍት ተለይተው ታውቀዋል ከዚህም ጉባኤ በኃላ ቅዱሳት መጻሕፍት በአንድ መድብል ተጠርዘው " መፅሐፍ ቅዱስ " ለመባል #በቅተዋል ፤ ይህ መፅሐፍ ቅዱስ #ሰማንያ #አሐዱ ( 81 ) #ቅዱሳት #መጻሕፍትን #የያዘ #መድብል #ነው ነገር ግን ሰማንያ አሐዱ ተብሎ በታተመው መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁሉም መፃሕፍት አልተካተቱም ምክንያቱም አንዳንዶቹ መጻሕፍት #በይዘታቸው #ትላልቅ #በመሆናቸው #ራሳቸውን #ችለው #እንዲቀመጡ #በመደረጉ #ነው።

#የኘሮቴስታንቱ #ዓለም #ግልፅ #ያልሆነለትና #ግራ #የተጋባው #ለመፅሐፍ #ቅዱስ #ታሪክ #ባዳ #ስለሆነ #ነው #ይኸውም #ያልተረዱት #ምንድን #ነው ? #ከተባለ #ከክርስቶስ ልደት 534 ዓመት በፊት ዕዝራና አብረውት የነበሩት ነቢያት ከባቢሎን ምርኮ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው #ጠፍተውና #ተቃጥለው #የነበሩትን #መፃሕፍት #ሲያሰባስቡ #በዕብራይስጥ የተፃፉትን #ብቻ #ነበር #ያሰባሰቡት ነገር ግን በሌላ ቋንቋ የተፃፉትን ቅዱሳት መፃህፍት ሳያሰባስቡ ቀርተዋል ለምሳሌ በ 1934 ዓ.አ {1947 እ.ኤ.አ} #በሙት #ባህር #አካባቢ #በቁምራን #ዋሻ ውስጥ #በዕብራይስጥ #ቋንቋቸው #የተፃፈው #መፅሐፈ_ሄኖክ #ተገኝቷል #ይሄ #የተገኝው #መፅሐፍ #በኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ቤተ #ክርስቲያን #ከሚገኘው #መፅሐፈ_ሄኖክ #ጋር #ተመሳክሮ #አንድ #ሆኖ #ተገኝቷል #በዚህም #ምክንያት #ዓለም #በእውነት #ኢትዮጵያ #የቅዱሳት #መፃህፍት #ማህደር #መሆኗን #ሳይወድ_በግድ #አምኖ #ተቀብሏል ፤ ይሄ የሚያሳየን በወቅቱ እነ ዕዝራ ሁሉንም ቅዱሳት መፃሕፍት ሰብስበው ለአይሁድ አለማስረከባቸውን ነው ፤ አይሁድ ለጊዜው እነዚህን ተጨማሪ መፃህፍት ከሌሎቹ መፃህፍትጋር አብረው ያልያዙአቸው ቢሆንም ከጊዜ በኃላ ግን ተገቢውን ክብር ሰተዋቸዋል ፤ አልተቀበሏቸውም ማለት ግን ፈፅሞ ስህተት ነው ምክንያቱም ከክርስቶስ ልደት 284 ዓመት በፊት #በበጥሊሞስ #ዘመነ መንግስት #ሰባው #ሊቃናት #መፅሐፍ #ቅዱስን #ከዕብራይስጥ #ወደ #ጽርዕ {ወደ ግሪክ} #ቋንቋ #የተረጎሙት #መፃሕፍት እነዚህን #ማጠቃለሉ #በቂ #ማስረጃ #ነው ፤ እነዚህ #ቅዱሳት #መፃሕፍት #በእናት #ቋንቋቸው #በዕብራይስጥ #ቋንቋ #ተፅፈው #ባያገኟቸው #ኖሮ #ከየት #አምጥተው #ይተረጉሙት #ነበር ? በ1959 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ግሪኮች ባሳተሙት መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ደግሞ ፦

መፅሐፈ #ጦቢት መፅሐፈ #መቃብያን መፅሐፈ መቃብያን #ካለዕ መፅሐፈ መቃብያን ካለዕ * ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን ( አራተኛ መፅሐፈ መቃብያካለዕ መመቃብያ ካለዕ መመቃብያካለዕ መፅሐፈ #ባሮክ #ይገኙበታል