Get Mystery Box with random crypto!

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት ዕቅድ ክንውን ሪፖርት ቀርቦ ከአስተዳደር ካ | ትምህርት ሚኒስቴር

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት ዕቅድ ክንውን ሪፖርት ቀርቦ ከአስተዳደር ካውንስል አባላት ጋር ውይይት ተደካሄደ።

በመድረኩ በትምህርት ሚኒስቴር አዲስ የተመደቡ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የቅበላ ዝግጅት እና የአካዳሚክ ካላንደር ሰነድ ቀርቦ ንግግር ተደርጎበታል።

ዩኒቨርሲቲው የ2014 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎን ለመቀበል እየተደረገ ያለውን ቅድመ ዝግጅት እና የቅበላ ጊዜን በተመለከተ «የተማሪዎች አቀባበልና አካዳሚክ ካላንደር» የተመለከተ ሰነድ በዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ልዩ አማካሪ በሆኑት መምህር ደሳለኝ ደርጋሶ ቀርቧል።

በቀረበው ሰነድ መነሻ፤ ዩኒቨርሲቲው በ2014 ዓ.ም 5000 የ1ኛ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ለመቀበል በየዘርፉ በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራ ሲከናወን መቆየቱን በቀረበው ሪፖርት ተብራርቷል።

በቀረበው አካዳሚክ ካላንደር መሰረት ፦

በ2014 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከሚያዝያ 27-28/2014 ዓ.ም ድረስ መሆኑ፤

በህገ ደንብ እና ተማሪዎች መከተል ስለሚገባቸው የስነ ምግባር ደንብ ገለጻ (Orientation) ሚያዝያ 29/2014 ዓ.ም እንደሚሰጥ፤

የመጀመሪያ ቀን፥ የመጀመሪያ ቀን ክፍለ ግዜ (DOCO) ግንቦት 01/2014 ዓ.ም እንደሚጀምር፤

የመጀመሪያ ሴሚስተር አጋማሽ ፈተና ከሰኔ 20-28/2014 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ እንዲሁም

የመጀመሪያ ሴሚስቴር የሚያበቃው እና ተማሪዎች ግቢ የሚለቁት ሰኔ 29 መሆኑን አስተዳደር ካውንስሉ የቀረበውን ሪፖርት ገምግሞ #አጽድቋል።
@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER