Get Mystery Box with random crypto!

በ2013 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና | ትምህርት ሚኒስቴር

በ2013 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚጠብቁ ተማሪዎች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።

ሁለቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በ 2014 ዓ.ም አዲስ የተማሪዎች ቅበላን ለማከናወን መጋቢት 07/2014 ዓ.ም ፈተና መፈተናቸው ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ በተለያዩ ምክንያቶች ምደባውን ለመግለፅ እንዳልተቻለ እና መጋቢት 17/2014 ምደባው የተለቀቀ መሆኑ ተገልጿል።

በሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች ኦፊሲያል ድህረ-ገጽ ላይ አድሚሽን ቁጥር በማስገባት ተማሪዎች መመልከት ይችላሉ ተብሏል።

www.aastu.edu.et / http://www.astu.edu.et

በሌላ በኩል የ2014 ዓ.ም አዲስ ገቢ አንደኛ አመት ቅድመ ምረቃ ተማሪዎች፣ ምዝገባ ሚያዝያ 28 እና 29/2014 ዓ.ም ሲሆን ትምህርት የሚጀመርበት ቀን እና በቅጣት የመመዝገቢያ ቀን ግንቦት 01/09/2014 ዓ.ም መሆኑ ተገልጻል።
@TIMIHIRT_MINISTER
@TIMIHIRT_MINISTER