Get Mystery Box with random crypto!

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሁለት ካምፓሶች በፀጥታ ችግር ተዘግተው ተማሪዎች እንዲሸጋሸጉ መደረጋቸው ተ | Tikvah-University

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሁለት ካምፓሶች በፀጥታ ችግር ተዘግተው ተማሪዎች እንዲሸጋሸጉ መደረጋቸው ተሰማ፡፡

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሥር የሚገኙት ዘንዘልማ እና ሰባታሚት ካምፓሶች በፀጥታ ችግር ምክንያት መዘጋታቸውን ሪፖርተር ዩኒቨርሲቲውን በመጥቀስ ዘግቧል።

በሁለቱ ካምፓሶች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ የግብርና፣ የጤና፣ የጂኦሎጂ እና የዲዛስተር ማኔጅመንት ተማሪዎች የፀጥታው ችግር እስኪቀረፍ ከተማ ውስጥ ባሉ ካምፓሶች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ማድረጉን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ብርሃኑ ገድፍ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በዘንዘልማ እና በሰባታሚት ካምፓሶች ውስጥ ይማሩ የነበሩ በርካታ ተማሪዎች ከተማ ውስጥ ያሉ ካምፓሶች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው፡፡

ዘንዘልማ እና ሰባታሚት ካምፓሶች በሚገኙባቸው አካባቢዎች የተኩስ ድምፅ በየጊዜው እንደሚሰማ የገለፁት ም/ፕሬዝዳንቱ፤ በተማሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከአንድ ወር በፊት ወደተለያዩ የተቋሙ ካምፓሶች እንዲዘዋወሩ መደረጉን ገልፀዋል፡፡

በከተማዋ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች ውስጥ በቂ ቦታ በመኖሩ ተማሪዎቹ ምንም ዓይነት መጉላላት ሳይደርስባቸው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ነው ብለዋል፡፡

አሁን ላይ ከሁለቱ ካምፓሶች ውጪ በሌሎች ካምፓሶች ላይ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር እንደሌለ ም/ፕሬዝዳንቱ ገልጸው፤ በባህር ዳር ከተማ ካለው አንፃራዊ ሰላም አኳያ በርካታ ተማሪዎች ምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡

ከሁለቱ ካምፓሶች ውጪ አለመረጋጋቱ የተሻሻለ ቢሆንም፤ አልፎ አልፎ የተኩስ ድምፅ እንደሚሰሙ ተማሪዎቹ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ የዘንድሮ ተመራቂዎች የምረቃ ቀን መቼ እንደሆነ እስካሁን እንዳልተነገራቸውም አክለዋል፡፡ #ሪፖርተር

@tikvahuniversity