Get Mystery Box with random crypto!

ታዳጊዎቹ የድረ-ገፅ አበልፃጊዎች ጎዶሊያስ ሙሉጌታ እና ሰላዲን መራዊ በአቤም ዩዝ አካዳሚ የሰባተ | Tikvah-University

ታዳጊዎቹ የድረ-ገፅ አበልፃጊዎች

ጎዶሊያስ ሙሉጌታ እና ሰላዲን መራዊ በአቤም ዩዝ አካዳሚ የሰባተኛ ክፍል ተማሪ ናቸው።

ታዳጊዎቹ የግለሰብ መረጃን ወይም 'CV' የሚያደራጅ ድረ-ገፅ አበልፅገዋል።

ድረ-ገፁ፤ ሰዎች ሥራን ለመቀጠር የሚያስገቡት የራስ መግለጫ 'CV'' በእጅ ስልካቸው ላይ እንዲያገኙና በማንኛውም ሰዓት ለሚፈልጉት ቀጣሪ ማስገባት የሚያስችል ነው።

ድረ-ገፁ የግለሰቡን የትምህርት ደረጃ፣ አድራሻ፣ ክህሎቶች እና የሰዎችን ምስክርነትን ማካተት የሚያስችል መሆኑን ታዳጊዎቹ ተናግረዋል።

ድረ-ገፁ የሰዎችን ብቻ ሳይሆን የድርጅቶችን መረጃ እንዲያስቀምጥ ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑንም ታዳጊዎቹ አስረድተዋል።

ታዳጊዎቹ በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም በተከፈተው የ'ስታርት አፕ' አውደ-ርዕይ ላይ ፈጠራቸውን አቅርበዋል። #ENA

@tikvahuniversity