Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፈው ወር ያጋጠመውን ችግር ተከትሎ ገንዘብ ያወጡ ወይም ያዘዋወሩና እስካ | Tikvah-University

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፈው ወር ያጋጠመውን ችግር ተከትሎ ገንዘብ ያወጡ ወይም ያዘዋወሩና እስካሁን ገንዘቡን ያልመለሱ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እስከ ዛሬ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም ድረስ ገንዘቡን እንዲመልሱ ዩኒቨርሲቲው ለመጨረሻ ጊዜ አሳስቧል፡፡

የወሰዱትን ገንዘብ ተመላሽ ያላደረጉ 55 ተማሪዎችን ሙሉ ስም፣ የተማሪ መለያ ቁጥር እና የትምህርት ክፍል ይፋ ያደረገው ዩኒቨርሲቲው፤ ለመጨረሻ ጊዜ በተሰጣቸው ዕድል ገንዘቡን በማይመልሱ ተማሪዎች ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው በጥብቅ አሳስቧል፡፡

@tikvahuniversity