Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሰሞኑን 'የተቋሙ የግዥ ሠራተኞች 882 ሺህ ብር ቅድመ | Tikvah-University

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሰሞኑን "የተቋሙ የግዥ ሠራተኞች 882 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ይዘው እንደጠፉ" በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የተዘገበው ትክክል አለመሆኑን ገለፀ።

የተቋሙ ሠራተኞች ከ2004 እስከ 2007 ዓ.ም ለተፈፀሙ ግዢዎች የተፈፀመን የብር 882,000 ክፍያ አስመልክቶ የተሠሩ ዘገባዎች ላይ ዩኒቨርሲቲው መግለጫ አውጥቷል።

"ክፍያውን ያከናወኑ የተቋሙ ሠራተኞች ለፈፀሙት ክፍያ በሕጉ መሠረት የማወራረድ ሥራ ማከናወን ሲገባቸው ይህን ሳያደርጉ ከተቋሙ የለቀቁ መሆናቸውን" መግለጫው አስታውሷል።

በመሆኑም "ጉዳዩ በ2008 ዓ.ም በተደረገ የኦዲት ምርመራ በኦዲት ግኝትነት የተያዘ ሲሆን፣ ዩኒቨርሲቲው ተገቢውን ዕርምጃ ለመውሰድ በጥረት ላይ እንደሚገኝ" የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) በሕ/ተ/ም/ቤት ለመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አብራርተዋል፡፡

"ይሁን እንጂ የፕሬዝዳንቱን ማብራሪያ የተለያዩ አካላት በማዛባት እና ከአውድ ውጭ በመተርጎም ለተለያየ የዜና ፍጆታ ሲጠቀሙት አስተውለናል" ብሏል መግለጫው፡፡

ክስተቱ ዛሬ ላይ የተፈፀመ ጉዳይ እንዳልሆነና በስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ተይዞ ክትትል እየተደረገበት የሚገኝ ጉዳይ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

(የዩኒቨርሲቲው መግለጫ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity