Get Mystery Box with random crypto!

#Update: በጄኔቫ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ለማሰባሰብ በተደረገው ስነ ስርዓት ሀገራት ከ600 ሚሊዮን | TIKVAH-MAGAZINE

#Update: በጄኔቫ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ለማሰባሰብ በተደረገው ስነ ስርዓት ሀገራት ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደሚሰጡ አስታወቁ

በኢትዮጵያ ለተከሰተው የሰብዓዊ ቀውስ አስቸኳይ 1 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማሰባሰብ በስዊትዘርላንድ ጄኔቫ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ሀገራት 630 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ለኢትዮጵያ እንደሚሰጡ አስታወቁ።

በዚህም አሜሪካ 253 ሚሊዮን ዶላር እንደምትሰት ቃል ስትገባ ዩናይትድ ኪንግደም 125 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በድምሩ ከ139 ሚሊየን ዶላር በላይ ለመስጠት ቃል ገብተዋል።

የመንግስታቱ ድርጅት በሚቀጥሉት 3 ወራት ብቻ ለኢትዮጵያ እርዳታ ለማቅረብ 1 ቢሊዮን ዶላር  እንዲሁም በሀገሪቱ በ2024 እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ 3.24 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልገኛል ማለቱ ይታወሳል።

@TikvahethMagazine