Get Mystery Box with random crypto!

#update: ' የ5 አመት ህፃን የደፈረው ግለሰብ ላይ ክስ መስርታ #በ6ወር እስራት እንዲቀጣ ያ | TIKVAH-MAGAZINE

#update: " የ5 አመት ህፃን የደፈረው ግለሰብ ላይ ክስ መስርታ #በ6ወር እስራት እንዲቀጣ ያስደረገችው ዐቃቤ ህግ ከስራ ታግዳለች " የቤንሻንጉል ክልል ፍትህ ቢሮ

በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ የ5 ዓመት ህፃን ልጅ ላይ በተፈፀመ የመድፈር ወንጀል የወንበራ ወረዳ ዐቃቤ ህግ በወንጀል ፈፃሚዉ ላይ ክስ መስርቶ ክርክር ከተደረገበት በኋላ የወንበራ ወረዳ ፍ/ቤት ጥፋተኛ የተባለዉን ግለሰብ #በ6ወር እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ ይታወሳል።

የቤንሻጉል ክልል ፍትህ ቢሮ የቅጣት ዉሳኔዉ ከተፈፀመዉ ወንጀል አንፃር አስተማሪነቱ አጠያያቂ እንደሆነና ለቅጣቱ ማነስ እንደ ምክንያትነት የሚጠቀሰዉ የክሱ አመሰራረት ክፍተት መሆኑን መገንዘቡን ገልጿል።

እናም የፍትህ ቢሮው የታችኛዉን መዋቅር ባሳተፈ መልኩ ዉጤታማ ስራ ሰርቶ የማስተካከያና የእርምት እርምጃ እስከሚሰጥ ድረስ ክሱን የመሰረቱት የወንበራ ወረዳ ዐቃቤ ህግ የሆኑት ወ/ሪት ዘወትር አበበ ቡሩሶ ከመጋቢት 20/2016 ዓ/ም ጀምሮ ከስራ ታግደው የሚሰጠዉን ዉሳኔ እንዲጠባበቁ ተወስኗል።

ምንም እንኳን ዐቃቤ ህግ በተሰጠዉ ዉሳኔ ይግባኝ የጠየቀ ቢሆንም ለተፈፀመዉ ወንጀል ተገቢዉን ዉሳኔ ከማሰጠት አኳያ በክስ አመሰራረቱ ላይ የተፈጠረዉን ክፍተት በጥናት ላይ ተመስርቶ በማረም ተገቢ እና ተመጣጣኝ ዉሳኔ ለማሰጠት እንደሚሰራም የፍትህ ቢሮው ገልጿል።

@TikvahethMagazine