Get Mystery Box with random crypto!

በወሊሶ ከአንድ ወጣት ሆድ ውስጥ 3 ትልልቅ ሚስማሮችን ጨምሮ መርፌ፣ ሽቦና 9 መፋቂያዎች በቀዶ ህ | TIKVAH-MAGAZINE

በወሊሶ ከአንድ ወጣት ሆድ ውስጥ 3 ትልልቅ ሚስማሮችን ጨምሮ መርፌ፣ ሽቦና 9 መፋቂያዎች በቀዶ ህክምና ተወገዱ

በወሊሶ አጠቃላይ ሆስፒታል ከ28 አመት ታካሚ ሆድ ውስጥ 1ብረት፣ 3 ቀጫጭን ሽቦዎች ፣ 3 ትላልቅ ሚስማሮች፣ 1 የልብስ መርፌ እና 9 መፋቂያዎችን በቀዶ ህክምና መውጣቱን የመርቲ ወረዳ ኮሚኒኬሽን አስታውቋል።

የተለያዩ ብረቶች በቀዶ ጥገና ከሆዱ የወጡለት ግለሰብ የአእምሮ ህመምተኛ መሆኑ ሲነገር የተወለደው በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን አማያ ወረዳ ነው። ታካሚው ህክምና ከተደረገለት በኋላ በአሁኑ ጊዜ በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል ተብሏል።

@TikvahethMagazine