Get Mystery Box with random crypto!

#ማስተካከያ የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን የጤና ባለሙያዎች የሙያ ስነ-ምግባር   ( | TIKVAH-MAGAZINE

#ማስተካከያ

የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን የጤና ባለሙያዎች የሙያ ስነ-ምግባር   (የህክምና ስህተት መከታተያ) ኮሚቴ በ7 ዓመት ውስጥ የታዩ አቤቱታዎችንና ጥቆማዎችን በመሰብሰብ ያጠናውን ጥናት አውጥቶ ነበር።

ባለሥልጣኑ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ እንዳሰፈረው በዚህ ጊዜ ውስጥ 282 አቤቱታዎች እንደቀረቡ እና  210 በትክክል እንዳታዩ ገልጿል።

ሆኖም ቀደም ሲል ከጥቆማዎቹ " ችግሮች ሲታዩም 64% ከእናቶች፣ ወሊድና ከማህፀን ጋር የተያያዘ " ነው ሲል አንስቶ ነበር።

የሥነ-ምግባር ኮሚቴ አባል የሆኑት የህክምና ባለሙያው አቶ እያያለም መለስ በፐርሰነት ሲቀመጥ ስህተት እንደነበረውና ስህተቱም በተቋሙ የፌስቡክ ገጽ ላይ ሲወጣ እንደሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

አሁን ላይ ተቋሙ መረጃውን ያስተካከለ ሲሆን በዚህም "ከ210 አቤቱታዎች 66 ወይንም 31.4% እናቶች ከወሊድና ከማህፀን ጋር የተያያዘ፣ ከ210አቤቱታዎች 41 ወይንም 20% ደግሞ በአጠቃላይ ሰርጀሪ ምክኒያት በሚያጋጥም የሞት አደጋ እና ከ210 አቡቱታዎች 32 ወይንም 15% በአጥንት ህክምና የሚመጡ አቤቱታዎች  እንደሆኑ  ገልጸዋል፡፡" ሲል አስተካክሎታል።

@TikvahethMagazine