Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ መተላለፉ ተገለፀ | TIKVAH-MAGAZINE

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ መተላለፉ ተገለፀ

ከአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዕውቅናና ውሳኔ ውጪ፣ በምክር ቤቱ ላይ የተለያዩ ሕገወጥ ተግባራት ተፈጽመዋል በማለት፣ የኦዲት ምርመራ እንዲደረግ የምክር ቤቱ ዳሬክተሮች ቦርድ ውሳኔ ማሳለፉን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ቦርዱ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በምክር ቤቱ ተፈጽመዋል ያላቸውን የተለያዩ ሕገወጥ ተግባር የሚያጣራ ኮሚቴ ያቋቋመ ሲሆን ተፈጽመዋል ከተባሉት ግድፈቶች መካከል፣ በተለይ የምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ከቦርዱ ዕውቅናና የምክር ቤቱ የአሠራር ፖሊሲ ውጪ፣ በርካታ የውጭ ጉዞዎችን በማድረግ፣ ሀብት እንዲባክን ተደርጓል መባሉን ዘገባው ጠቅሷል።

በዚህም በመቶ ሺዎች የሚገመት የውጭ ምንዛሪ ወጪ ተደርጓል የተባለ ሲሆን  ከ15 ሺሕ በላይ የሚሆነው የምክር ቤቱ አባላት ሀብት እንዲባክንና ኃላፊዎቹ ሕገወጥ የሠራተኞች ቅጥር ማካሄድ፣ ሠራተኞች ማሰናበት፣ የደረጃ ዕድገት መስጠት ከቦርዱ ዕውቅና ውጪ የተፈጸሙ የብልሹ አሠራር ሒደቶች መሆናቸውን ቦርዱ ገልጿል ተብሏል።

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤና ዋና ጸሐፊው አቶ ሺበሺ ቤተ ማርያም፣ ተፈጠሩ የተባሉትን ችግሮች በተመለከተ ቦርዱ እንዲያጣራ ውሳኔ ማሳለፉን አረጋግጠው፣ ነገር ግን የቀረበባቸው አቤቱታና ቅሬታ ትክክል  አለመሆኑንና ምክር ቤቱ ሕግና ሥርዓቱን ጠብቆ እየሠራ ስለመሆኑ፣ በበቂ ማስረጃ ማሳየት እንደሚቻል መናገቸውም ነው የተገለፀው።

@TikvahethMagazine