Get Mystery Box with random crypto!

#UNICEF #ETHIOPIA በኢትዮጵያ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናት እንዲሁም 350 ሺ ነፍሰ ጡር | TIKVAH-MAGAZINE

#UNICEF #ETHIOPIA

በኢትዮጵያ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናት እንዲሁም 350 ሺ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች ለከፋ የምግብ እጥረት ይጋለጣሉ ሲል ዩኒሴፍ አስጠነቀቀ።

በ2024 በኢትዮጵያ ወደ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናት እና ወደ 350,000 ነፍሰ ጡር እንዲሁም የሚያጠቡ እናቶች ለከፋ የምግብ እጥረት የሚጋለጡ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) በትላንትናው እለት ባወጣው መግለጫ አስጠንቅቋል።

የዩኒሴፍ ምክትል ስራ አስፈፃሚ ቴድ ቻይባን በኢትዮጵያ ለ5 ቀናት ባደረጉት ጉብኝት በመላ ሀገሪቱ እየደረሰ ያለውን የከፋ ሰብአዊ አደጋ ለመከላከል አለም አቀፉ ማህበረሰብ ለህጻናት እና ቤተሰቦች የሚያደርገውን ድጋፍ በአፋጣኝ እንዲያጠናክር አሳስበዋል።

ቻይባን በድርቅ ከተጠቁት አካባቢዎች ውስጥ የትግራይ ክልልን የጎበኙ ሲሆን በክልሉ የምግብ ዋስትና ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ዜጎች ችግሩን ሊቋቋሙ የሚችሉበት መንገዶች መሟጠጣቸውንና በሀገሪቱ ውስጥ የኮሌራ፣ የኩፍኝ፣ የዴንጊ ትኩሳት እና የወባ ወረርሽኝ መከሰቱ የህብረተሰቡን የጤና ሁኔታ የበለጠ እንዳወሳሰበው ጠቁመዋል።

" ኢትዮጵያ በርካታ ቀውሶች ተጋርጠውባታል ያሉት ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚው " በኤልኒኖ ምክንያት የተከሰተውና በሰሜን፣ በመካከለኛው እና በደቡብ ኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ በሚሊዮን በሚቆጠሩ ህጻናት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው" ብለዋል።

በዚህም በ 2024 ወደ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናት በከፍተኛ የምግብ እጥረት እንደሚሰቃዩ እና 350,000 የሚጠጉ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንደሚገጥማቸው ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልፀው አለም አቀፉ ማህበረሰብ ለህጻናት እና ቤተሰቦች የሚያደርገውን ድጋፍ በአፋጣኝ እንዲያጠናክር አሳስበዋል።

@TikvahethMagazine