Get Mystery Box with random crypto!

በሞያሌ በተከሰተ የኮሌራ በሽታ የአምስት ሰዎች ህይወት አለፈ። በኢትዮጵያና በኬንያ አዋሳኝ በሆነ | TIKVAH-MAGAZINE

በሞያሌ በተከሰተ የኮሌራ በሽታ የአምስት ሰዎች ህይወት አለፈ።

በኢትዮጵያና በኬንያ አዋሳኝ በሆነችው ሞያሌ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ የተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝ የአምስት ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል። ከዚህ ውስጥ ሁለቱ ሞያሌ በሚገኘው የኮሌራ ህክምና ማዕከል ከገቡ በኋላ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ሌሎቹ ወደ ማዕከሉ ሳይደርሱ ነው ህይወታቸው ያለፈው።

በቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ የጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ቦሩ ሁካ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጹት በየቀኑ 15 ሰዎች በበሽታው እየተያዙ መሆኑን አንስተው አሁን ላይ በማዕከሉ 50 የሚሆኑ ታማሚዎች ህክምና እየተደረገላቸው ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ በሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች የተከሰተውን ከባድ ድርቅ ተከትሎ በተለያዩ ዞኖች በተስተዋለው የኮሌራ ወረርሽኝ በመስፋፋቱ እስካሁን 44 ሰዎች ሕይወት ማለፉን በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና አደጋ አስተባባሪው አቶ መስፍን ወሰን ለDW ተናግረዋል።

የዓለም ጤኛ ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው እስከ ጥር መጨረሻ ድረስ እስካሁን 18 ሀገራት የኮሌራ መከሰትን ሪፖርት አድርገዋል። በኢትዮጵያም ባለፈው ዓመት መጨረሻ በሽታው ሪፖርት የተደረገ ሲሆን ከዛን ጊዜ ጀምሮ 1,896 ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን የኦቻ ሪፖርት ያሳያል።

@tikvahethmagazine