የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፲ኛ ዓመት በዓለ ሲመት ዛሬ ተከብሯል። የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያ | TIKVAH-MAGAZINE

Picture 1 from TIKVAH-MAGAZINE 2023-03-03 13:44:37
Picture 2 from TIKVAH-MAGAZINE 2023-03-03 13:44:37
Picture 3 from TIKVAH-MAGAZINE 2023-03-03 13:44:37
Picture 4 from TIKVAH-MAGAZINE 2023-03-03 13:44:37
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፲ኛ ዓመት በዓለ ሲመት ዛሬ ተከብሯል።

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖትን 10ኛ ዓመት በዓለ ሢመት ዛሬ የካቲት 24 ቀን 2015 ዓ/ም  በመንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከብሯል።

በትላንትናው ዕለትም ፲ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በማስመልከት ዜና መዋዕል ዘብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክና ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የተሰኙ መጽሐፍት ተመርቀዋል።

መጽሐፍቱ የቅዱስነታቸውን የሕይወት ታሪክ፣ ባለፉት ፲ ዓመታት በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገራት ያከናወኗቸውን ዋና ዋና ሥራዎችን፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎችን፣ ቤተ ክርስቲያን ባለፉት ፲ ዓመታት በስኬት ያከናወነቻቸው ዋና ዋና ተግባራት እና የገጠሟትን ተግዳሮቶች ተከትሎ በቅዱስ ፓትርያርኩ የተላለፉ መልዕክታትን አጠቃሎ የያዘ መሆኑ ተገልጿል።

መጻሕፍቱን በውጪው ዓለም የሚገኙ ምዕመናን  በቀላሉ አግኝተው ማንበብ ይችሉ ዘንድም በቤተ ክርስቲያን ድረ ገጽ https://www.eotceth.org  ላይ እንዲጫን መደረጉን የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አሳውቋል።

ፎቶ: ተሚማ

@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE

TIKVAH-MAGAZINE

@tikvahethmagazine
192.47K ተመዝጋቢዎች
ዜና ምድብ
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያና የመረጃ መለዋወጫ መድረክ ነው። በ 251913134524 ላይ ያግኙን። ለማ...