Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ ጤና መድህን ትግበራ 10ኛ ዓመት ዛሬ ተከብሮ ውሏል የኢትዮጵያ ጤና መድህን ትግበራ 1 | TIKVAH-MAGAZINE

በኢትዮጵያ ጤና መድህን ትግበራ 10ኛ ዓመት ዛሬ ተከብሮ ውሏል

የኢትዮጵያ ጤና መድህን ትግበራ 10ኛ ዓመት ክብረ በዓል እና የማህበረሰብ አቀፍ  የጤና መድህን ብሔራዊ ምክር ቤት ይፋዊ የስራ ማስጀመሪያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ዛሬ ተካሂዷል።

ምን ምን ነጥቦች ተነሱ፦

- በሀገራችን 40 በመቶ ዜጎችቻችን ወደ ህክምና የማይሄዱበት ምክንያት የመታከሚያ ገንዘብ ማጣት መኾኑ ተጠቁሟል።

- የማህበረሰብ አቀፍ የጤና አገልግሎት መርሀ ግብር አብዛኛውን አርሶ አደር የሕብረተሰብ ክፍል የሚያቅፍ ወሳኝ የሆነ የጤና አገልገሎት ተደራሽነትን የሚያረጋግጥ ነው ተብሏል።

- አገልግሎቱ በሁሉም ክልሎችና  ከተማ አስተዳደሮች በ894 ወረዳዎች ተግባራዊ በማድረግ 45 ሚሊዮን ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ተገልጿል።

@tikvahethmagazine