ሁለተኛው ዙር የትምህርት መፅሀፍት ማሰባሰብ ዘመቻ ዛሬ ይጀመራል። በዚህ ዙር በጦርነት የተጎዱ ትምህርት ቤቶች ከሚያስፈልጋቸው ቁሳቁስ አንፃር መማሪያ መፅሀፍ ብቻ ሳይሆን ፦ + ነጭ ወረቀት + ያገለገለ ፕሪንተር + የፕሪንተር ቀለም + ማንኛውም አይነት ያገለገለ ኮምፒዩተር መስጠት ይቻላል። ውድ ቤተሰቦቻችን በመጀመሪያው ዙር በጥቂት ቀናት ዘመቻ 8 ሺህ ገደማ መፅሀፍ መሰባሰቡ አይዘነጋም አሁን በትንሹ 30 ሺህ መፅሀፍ ለማግኘት ታቅዷል። መስጠት የሚቻለው መፅሀፍ ፦ - ከ1-8 #አጋዥ_መፅሀፍ_ብቻ - ከ9-12 ማኛውም መደበኛ (ቴክስት) እና አጋዥ መፅሀፍ በተጨማሪ ፦ ከከተማ ወጣ ብሎ ለሚገኝ የህዝብ ቤተመፅሀፍ ማንኛውም አይነት አሉታዊ መልዕክት የማያስተላልፍ ልብወለድ መፅሀፍ መለግስ ይቻላል። #አዲስ_አበባ ስልክ ፦ 0919743630 በቅርብ ቀናት በሀዋሳ ተመሳሳይ ዘመቻ ይኖራል። ማሳሰቢያ ፦ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ የገንዘብ ድጋፍ የሚሰበሰብ ባለመሆኑ ከላይ የተዘረዘሩትን ቁሳቁሶች #የመግዛት_አቅም ያላችሁ ቁሳቁሶቹን ገዝታችሁ ማበርከት ትችላላችሁ። የማሰባሰብ ስራው የሚያበቃበት ቀን ከየካቲት 30 በፊት። @tikvahethiopia 18.1K views07:00