Get Mystery Box with random crypto!

#ኦሮሚያ በኦሮሚያ ክልል በ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ውስጥ 900 የትራፊክ አደጋ | TIKVAH-MAGAZINE

#ኦሮሚያ

በኦሮሚያ ክልል በ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ውስጥ 900 የትራፊክ አደጋዎች ተከስተዋል።

በደረሰዉ አደጋ የ367 ሰዎች (በቀን በአማካይ ከ4 ሰው በላይ)ህይወታቸዉን ሲያጡ፣ 286 ሰዎች ላይ ከባድ እና በ273  ቀላል የአካል ጉዳት ተመዝግቧል፡፡ እንዲሁም ከ92 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የንብረት ውድመት ደርሷል፡፡

በከተማ ደረጃ በአዳማ፣ ሻሸመኔ፣ዱከም ፣ቡራዩ ፣ሰበታ ፣ ሱሉልታ ከፍተኛ አደጋ የተመዘገበባቸዉ ከተሞች ሲሆኑ 87 በመቶ የሚሆነው አደጋ በቀኑ ክፍለ ጊዜ የደረሰ ሲሆን 13 በመቶ የሚሆነው ደግሞ በሌሊቱ ያጋጠሙ ናቸው ተብሏል፡፡

ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት፣ ከፍጥነት ወሰነ በላይ ማሽከርከር ፣ የአሸከርካሪዎች ጥንቃቄ ጉድለት፣ ያለ እረፍት ማሸከርከር፣ምልክቶችን አለማክበር፣ርቀትን ጠብቆ አለማሽከርከር የአደጋዎቹ መንስኤ ናቸው ተብሏል፡፡

በ2015 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የደረሰው የትራፊክ አደጋ ካለፈው 2014 ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር  በ44 የሞት አደጋ ቀንሷል።

@tikvahethmagazine