Get Mystery Box with random crypto!

#የዛሬ (ግንቦት 15/2014) የአማራ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ፤ በክልሉ ከ4 ሺህ በላይ ተ | TIKVAH-MAGAZINE

#የዛሬ (ግንቦት 15/2014)

የአማራ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ፤ በክልሉ ከ4 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታውቋል። የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳሳለኝ ጣሰው እንደገለጹት በቁጥጥር ሥር ከዋሉት 40 የሚሆኑት ከዚህ ቀደም በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብለው ፍርድ የተላለፈባቸው መሆናቸውን የጠቀሱ ሲሆን 210 የሚሆኑት ደግሞ በነፍስ ግድያ የተጠረጠሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ከትላትን በስቲያ፤ በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ በሚገኘው ስደተኛ መጠለያ ጣቢያና በመርከስ ቀበሌ ለጊዜው ማንነታቸው አልታወቀም በተባሉ ግለሰቦች የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

"በዓለማችን ያለው ቀውስ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ብቻ አይደለም። በዓለም ዙሪያ ያሉ ባልደረቦቻችን በዲሞክራቲክ ኮንጎ ለኢቦላ ወረርሽኝ፣ በአፍጋኒስታን፣ በኢትዮጵያ፣ በሶማሊያ፣ በደቡብ ሱዳን፣ በሶሪያ፣ በዩክሬንና በየመን ደግሞ ውስብስብ ለሆነ ሰብዓዊ ቀውስ ምላሽ ለመስጠት እየሰሩ ነው" | ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደባህሬን አቋርጦ የነበረውን በረራ በሳምንት 3 ጊዜ ከግንቦት 24 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የሚጀምር መሆኑን ገልጿል።

"እንደማንኛውም ሀገር እኛም በቫይረሱ [Mokeypox] ስርጭት ስጋት አለን። በኢትዮጵያ የመግቢያ እና መውጫ በሮች ላይ የተለመደው ክትትል እየተደረገ ይገኛል። በሀገሪቱ የየብስ እና የአየር ትራንስፖርት መግቢያ እና መውጫ ላይ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ እና ወደ ሌሎች ሀገራት እንዳይሄድ የተላላፊ በሽታዎች ክትትል እየተደረገ ነው።'' | አቶ ዘውዱ አሰፋ በኢ/ህ/ጤ/ኢ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና መረጃ ስርዓት አስተዳደር ዳይሬክተር

የቻን የአፍሪካ ዋንጫ በአስራ ስምንት ብሄራዊ ቡድኖች መካከል እንዲካሄድ ከውሳኔ ላይ መድረሱ ተገልጿል። ካፍ የተሳታፊ ሀገሮችን ብዛት በሁለት ማሳደጉ የተገለፀ ሲሆን ከቀናት በኋላ ግንቦት 18 የቻን የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች የእጣ ድልድል እንደሚወጣ ተነግሯል። የቻን የአፍሪካ ዋንጫ በሰሜን አፍሪካዋ ሀገር አልጄሪያ ከታህሳስ 30 እስከ ጥር 23 ድረስ 2015 ድረስ እንደሚካሄድ ተዘግቧል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot