Get Mystery Box with random crypto!

#Update ባይደን ፊርማቸውን አኑረዋል ፤ ቲክቶክ ' ፍርድ ቤት እንተያይ ' ብሏል። የአሜሪ | TIKVAH-ETHIOPIA

#Update

ባይደን ፊርማቸውን አኑረዋል ፤ ቲክቶክ " ፍርድ ቤት እንተያይ " ብሏል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በባይት ዳንስ ባለቤትነት ያለው " #ቲክቶክ " ድርሻው ለአሜሪካ ኩባንያ ተሽጦ ከቻይና ካልተፋታ በመላው አሜሪካ #እንዲታገድ የቀረበላቸው ረቂቅ ሕግ ላይ ፊርማቸውን በማኖር ሕግ ሆኖ  እንዲወጣ አድርገዋል።

" ቲክቶክ " ድርሻው ለአሜሪካ ኩባንያ እንዲሸጥ የተሰጠው ጊዜ ከ9 ወር እስከ 1 ዓመት ብቻ ነው።

በዚህ ጊዜ ይህንን ካላደረገ #እስከወዲያኛው ከአሜሪካ እንደሚታገድ ተገልጿል።

አሁን በአሜሪካ ብቻ 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት " ቲክቶክ " ሙሉ በሙሉ የመታገዱ ነገር #እውን ወደ መሆኑ ተቃርቧል።

የቲክቶክ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ሹ ዚ ቼው ፥ " የትም አንሄድም። ለመብታችን በፍርድ ቤት እንታገላለን። ሀቁ እና ህገ መንግስቱ ከጎናችን ናቸው፣ እናሸንፋለን ብለን እንጠብቃለን " ሲሉ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፤ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለዩክሬን ፣ እስራኤል እና ታይዋን የቀረበው የ95 ቢሊዮን ዶላር የድጋፍ ጥቅል ረቂቅ ሕግ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል።

@tikvahethiopia