Get Mystery Box with random crypto!

' ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ መላክ እንጀምራለን፤ ... የንግድ ቻርተር አውሮፕላኖችንም ተከ | TIKVAH-ETHIOPIA

" ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ መላክ እንጀምራለን፤ ... የንግድ ቻርተር አውሮፕላኖችንም ተከራይተናል " - ጠ/ሚር ሪሺ ሱናክ

ዩናይትድ ኪንግደም በቁጣዮቹ ከ10 እስከ 12 ሳምንታት ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ #ሩዋንዳ መላክ ትጀምራለች።

የዩናይትድ ኪንግደም ፓርላማ ስደተኞች/ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ለመመለስ የተያዘውን እቅድ መጀመር የሚያስችለውን " የሩዋንዳ እቅድ " የተሰኘውን ረቂቅ ሕግ ትላንት አጽድቋል።

ጠ/ሚር ሪሺ ሱናክ፥ " በቀጣዮቹ ከ10 እስከ 12 ሳምንታት ባለው ጊዜ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ መላክ እንጀምራለን " ብለዋል።

ለዚህም ፤ የንግድ ቻርተር አውሮፕላኖች ኪራይ መፈጸሙና ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የሚወስዱ ሰራተኞችም መሰልጠናቸው ተነግሯል።

52,000 ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ምስራቅ አፍሪካዋ ሩዋንዳ ይዘዋወራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በቅርብ አመታት ፦
- #ከአፍሪካ ፣
- ከመካከለኛው ምስራቅ
- ከኢስያ ጦርነት እና ድህነት የሚሸሹ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ዩናይትድ ኪንግደም ገብተዋል።

እነኚህ ስደተኞች በህገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት በትንንሽ ጀልባዎች ተጉዘው ነው ዩናይትድ ኪንግደም የሚገቡት። #ሮይተርስ

@tikvahethiopia